በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል Different Types of Bolt with Nut በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የሀገር ውስጥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/Re‐15/2017
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል Different Types of Bolt with Nut በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የ2018 ዓ.ም የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት (ከሆኑ)፣ የታክስ ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የታክስ ክሊራንስ ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዝ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅደመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒከ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር እስከ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
ስልክ 0114420216
ፋክስ 0114420688
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
Tender details
- Deadline: 2026-05-12
- Publishing entity: Mugher Cement Factory
- Bid bond: 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
- Bid document price: 575.00 ብር
- Published: May 02, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.