በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን የሆሣዕና ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ላሉት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ አወዳድሮ መግዛት/ለማሰፋት/ ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ዙር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ዲስትሪክት 003/2018

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን የሆሣዕና ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ላሉት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ አወዳድሮ መግዛት/ለማሰፋት/ ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን የ2018 ዓ/ም ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀትእና ወረቀትእና በአቅራቢነት ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ ‹‹ኦርጅናል›› እና ‹‹ኮፒ›› በማያያዝ እና የጨረታ ማስከበርያውንም በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከዲስትሪክቱ የፋይናንስና ሎጅስቲክስ ደጋፊ የሥራ ሂደት መግዛት ይችላሉ።

4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነት ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ማቅረቢያና ተያያዥ ዶክመንቶችን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሆሣዕና ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በዚያኑ ቀን 10፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10% የማስያዝ ግዴታ ይኖርበታል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።

7. በጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ቢድ ቦንድ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል።

8. አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ እስከ 5 (አምስተኛ) ቀን ድረስ ውል ማስከበሪያ አስይዞ ውል የማይፈፅም ከሆነ ያሲያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

9. ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

10. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

የዲስትሪከት ጽ/ቤት የሥልክ ቁጥር 046-555-2348፣ 046 555-2349

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን የሆሳዕና ዲስትሪክት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-18
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00
  • Bid opening: 2026-05-18 16:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡30
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን የሆሳዕና ዲስትሪክት ጽ/ቤት
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: May 03, 2026
  • Posted at: 2026-05-04T08:25:57.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders