አዲስ ባንከ አ.ማ አልሙኒየም ፓርትሽን፣ መስታወት እና ጂፕሰም ቦርድ ባለበት ሁኔታ እና አልሙኒየም ሼልፍ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የሸያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ ባንከ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ጨረታው በሚከናወንበት ቦታ አዲስ ባንከ ዋና መ/ቤት ዝቋላ ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ በመገኘት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
መግለጫ |
መለኪያ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ በጥቅልከቫት በፊት ብር |
ጨረታ የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አልሙኒየም ፓርትሽን፣ መስታወት እና ጂፕሰም ቦርድ ባለበት ሁኔታ |
በጥቅል |
2,590,912.23 |
ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 |
|
2 |
አልሙኒየም ሼልፍ ባለበት ሁኔታ |
በጥቅል |
448,393.43 |
ማሳሰቢያ፡-
1. ንብረቶቹን ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ግንቦት 6፣7 እና 8 ቀን 2018ዓ.ም አዲስ ባንክ እናት ባንክ ጀርባ ኢትስዊች ህንጻ 4ኛ እና 5 እኛ ፎቅ በመገኘት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በመገኘት ማየት ይቻላሉ። ስልክ ቁጥር 011 557 0319
2. ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጓቸውን ንብረቶች ዝርዝር ሁኔታ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚገኝ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በአዲስ ባንክ አ.ማ ባምቢስ ኖከ ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንጻ ዓብይ ቅርንጫፍ በመክፈልና ደረሰኙን በመያዝ ከእናት ባንክ ጀርባ ኢትስዊች ህንጻ አምስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የግዥና ፋስሊቲ አስተዳደር መምሪያ ከሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡00-6፡00፣ ከስዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት 2፡00- 6፡00 ማግኘት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ግንቦት 12 ቀን እስከ ቀኑ 7፡30 ድረስ አዲስ ባንከ ዋና መ/ቤት ዝቋላ ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. የጨረታው ማስከበሪያ የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ /ሲ.ፒ.ኦ/ በጨረታው ዕለት ይዞ በመምጣት መወዳደር ይቻላል።
5. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል ንብረቶቹ ከተገጠሙበት ቦታ ነቅሎ ማንሳት ይኖርበታል። በነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ለጨረታ ያስዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ባንኩ ሌላ አማራጭ ይወስዳል። ጨረታውን ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የክፍያ ሰነድ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
6. ጨረታው ግንቦት 12 ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ ባንክ ዋና መ/ቤት ዝቋላ ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ ይከፈታል።
7. ለበለጠ ማብራሪያ አዲስ ባንክ ኢማ ዋና መ/ቤት በስልክ ቁጥር 011 557 0319 ደውሎ መረዳት ይቻላል።
8. ባንኩ ንብረቱን ለመሸጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
አዲስ ባንክ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-05-20
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-05-20 14:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: May 03, 2026
- Posted at: 2026-05-04T08:29:21.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.