የወንዶ ትራንስፖርት ኩባንያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003/2018
የወንዶ ትራንስፖርት ኩባንያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዳቶ ኦይል ሊቢያ የነዳጅ ማድያ አጠገብ በሚገኘው ቢሯእችን ገቢ ውስጥ ተሽከረካርዎቹን በማየትና የጨረታ ሰነድ በመናሃሪያ ክ/ከተማ ዳእቴ ሆቴል ፍትለፍት ከሚገኘው ወንዶ ንግድ እና ኢንቨስትሜንት ህንጻ 1ኛ ፎቅ ከሚገኘው ከግ/ፋ/ን አስተዳደር መምሪያ በብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በማወዳደሪያ ሰነድ ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የተጫራቹን ስም እና አድራሻ በመጻፍ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት አየር ላይ ውሎ በ8ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በ8፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/መምሪያ ቢሮ በግልጽ ይከፈታል. ሆኖም 8ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል።
- ተጫራቹ በጨረታ አሸንፎ የገዛውን ተሽከርካር ከፍያውን በ05 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት፤
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የተከፈለ መሆኑን የሚያረጋግፕ መረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ማናቸውም ተጫራቾች ላሸነፈባቸው ተሽከርካርዎች ሙሉ ክፍያ ፈጽሞ እስከሚያነሳ ድረስ ለውሉ ማስፈጸሚያ ዋስትና እንዲሆን ለጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፈበት ዋጋ 10% ገንዘብ ማስያዝ አለበት።
- ማናቸውም ተጫራች ሌሎች አስገዳጅ ሁኔታዎች እስካልተፈጠሩ ድረስ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ሙሉ ክፍያ ከፍሎ በአምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማንሳት ግዴታ አለበት።
- ማናቸውም ተጫራቾች ከተጫረተ በኃላ በሌሎች ተጫራቾቾ ተበልጦ ቢሸነፍ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ይመለስለታል።
- ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ ለመቀበል ወይም ላለመቀበል ወይም ለመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 222 09024 ወይም 09 16 86 05 65/ 09 12 78 09 26 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የመ/ቤቱ አድራሻ፦ ሀዋሳ መናኸሪያ ከ/ከተማ ዳእቴ ካፌና ሬስቶራንት ፊትለፍት በሚገኘው ወንዶ ኩባንያ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ።
የወንዶ ትራንስፖርት ኩባንያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-11
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት አየር ላይ ውሎ በ8ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-11 14:10
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት አየር ላይ ውሎ በ8ኛው ቀን ከቀኑ 8፡10 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Wendo Transport Company P.L.C.
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: May 03, 2026
- Posted at: 2026-05-04T08:34:23.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.