ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ዕቃዎች የጨረታ ሽያጭ
የጨረታ ቁጥር ግፋዳንአአ/004/2018
ማስታወቂያ ቁጥር 004/2018
ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ዕቃዎቹን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቦሌ መንገድ ጌቱ ኮሜርሽያል ሴንተር ህንፃ ጎን ከሚገኘዉ የባንኩ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407-8-1 (ንብረት እና አቅርቦት አስተዳደር ዋና ክፍል) በመውሰድ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላል።
1. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎች አቃቂ ዩኒሳ አደባባይ አካባቢ (ከአንበሳ ቆርቆሮ ፋብሪካ - ጎን) ከሚገኘው የባንኩ መጋዘን በአካል ተገኝተው በማየት ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለፀዉ የባንኩ ዋና መ/ቤት አድራሻ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
2. ጨረታዉ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ላይ ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ላይ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል።
3. ለጨረታው ማስከበሪያ የብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ሲ.ፒ.ኦ በኦሮሚያ ባንክ ኢማ ስም አስርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
4. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
ብዛት |
|
1 |
የተለያዩ ያገለገሉ ፕሪንተሮች /Printers/ |
20 |
|
2 |
የተለያዩ ያገለገሉ ዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተሮች |
17 |
|
3 |
የተለያዩ ያገለገሉ እስካነሮች /Scanners/ |
20 |
|
4 |
እስታብላይዘር /Stabilizer/ |
3 |
|
5 |
የተለያዩ ያገለገሉ የፎቶ ኮፒ ማሽኖች |
6 |
|
6 |
የተለያዩ ያገለገሉ የገንዘብ መቁጠሪያና መለያ ማሽኖች |
49 |
|
7 |
የተለያዩ ያገለገሉ የፋክስ ማሽኖች |
23 |
|
8 |
የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሪክ ካልኩሌተሮች |
19 |
|
9 |
ያገለገሉ የገንዘብ ማስቀመጫ ሰጥኖች |
8 |
|
10 |
ያገለገሉ የአየር ማቀዝቀዣ /Ventilator/ |
10 |
|
11 |
ያገለገሉ የመተያቢያ ማሽን /Type writer/ |
4 |
|
12 |
ያገለገለ የዉኃ ማጣሪያ (Water Filter) |
1 |
|
13 |
ያገለገሉ ባለ ረጅም፣ መካከለኛ፣ አጭር መደገፊያ እና የቴለርስ አስቱል ተሽከርካሪ ወንበሮች |
83 |
|
14 |
ያገለገሉ ባለ አንድ መቀመጫ የደንበኛ ወንበሮች |
73 |
|
15 |
ያገለገሉ የቡና የፎቶ ኮፒ ማስቀመጫ እና የገንዘብ መለያ ጠረጴዛዎች |
13 |
|
16 |
የጥበቃና የጄነሬተር መጠሊያዎች/ ቤቶች |
12 |
|
17 |
ያገለገሉ ባለ ሶስት /03/ መቀመጫ የደንበኛ ወንበሮች |
5 |
|
18 |
ያገለገሉ ባለ 4-መሳቢያና ላቴራል የፋይል ማስቀመጫ ካቢኔቶች |
5 |
|
19 |
የተለያዬ መጠን ያላቸዉ ዉጭ ሀገር ገንዘብ ምንዛሪ ማስታወቂያ አነስተኛ ሰሌዳዎች |
15 |
|
20 |
የተለያዬ መጠን ያለቸዉ ያገለገሉ የቅ/ፍ ስም ማስተወቂያ የአቅጣጫ ማሳያ ሰሌዳዎች |
8 |
|
21 |
የተለያዩ የገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎች |
57 |
|
22 |
ያገለገሉ የፍሎረሰንት አቃፊዎች (Fluorescent holders) |
50 |
|
23 |
የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ዕቃዎች (Spare parts) |
ባለበት |
|
24 |
ያገለገሉ የቤት ወለል ንጣፍ ታይሎች (Floor tiles) |
ባለበት |
|
25 |
ያገለገሉ የእብነበረድ ቁርጥራጮች |
ባለበት |
ኦሮሚያ ባንክ አማ
መደበኛ ስልክ ቁጥር- 011 557-2037/ 011 462-4919
ተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር፡- 09 12-73-64-32/ 09 11-80-23-54
Tender details
- Deadline: 2026-05-15
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-05-15 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Bank S.C.
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 /ሁለት መቶ/
- Published: May 03, 2026
- Posted at: 2026-05-04T09:54:23.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.