አመልድ ኢትዮጵያ ልዩ ልዩ መጠን ያላቸው የፌሮ ብረቶችን ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ልዩ ልዩ መጠን ያላቸው የፌሮ ብረቶችን ለመሸጥ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
አመልድ ኢትዮጵያ በተሻሻለዉ የኢትዮጵያ የሲቨል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 በአንቀጽ 61(4) ማንኛዉም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት በስሙ በባለቤትነት የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት የመሆን፤ንብረት የማስተዳደርና የማስተላለፍ መብት አንዳለዉ እና በመመሪያ ቁጥር 850/2014 ስለንብረት ማስወገድ በተደነገገ መሠረት አመልድ ኢትዮጵያ በዋናው መ/ቤትና በተለያዩ ፕሮጀክቶች የግንባታ ስራ ላይ የተረፉ የተለያየ መጠን ያላቸው የፊሮ ብረቶችን በ11 (አስራ አንድ) ምድቦች በመመደብ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
1. ከአመልድ ኢትዮጵያ ሰራተኞች ውጭ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው
2. ተጫራቾች የምድቦችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ባህርዳር አመልድ ኢትዮጵያ ቢሮ ቁጥር 106 እና አዲስ አበባ አመልድ ኢትዮጵያ ቅ/ጽ/ቤት ለጋሀር አመልድ ህንፃ አማራ ባንክ ዋናው መ/ቤት ከሚገኝበት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ድረስ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ አስረኛው ተከታታይ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
4.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ምድብ መነሻ ዋጋ መሰረት በማድረግ የጠቅላላ ዋጋዉን 10% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በአመልድ ኢትዮጵያ ስም ማስያዝ አለባቸው።
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን መጫረቻውን ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ባህርዳር በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 106 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እሰከ አስርኛው ተከታታይ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህርዳር ቢሮ ቁጥር 106 በጋዜጣ አየር ላይ በዋለ አስረኛው ተከታታይ የሥራ ቀን በ4፡00 ስዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ይከፈታል።
7. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ ብረቶችን በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በተገለፀዉ ቦታ ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እሰከ አስረኛው ተከታታይ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ብረቱ ባለበት ባህርዳር አመልድ ኢትዮጵያ ጋራጅ በመሄድ ማየት ይችላሉ።
8. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነዉ በተቀመጠው የብረት ምድብ ነጠላ መሰረት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ይሆናል። ተመሳሳይ የፌሮ ብረት መጠን ዓይነት ያላቸውና በአንድ ላይ የተቀመጡትን ፌሮ ብረት አሸናፊ የሆኑ ግለሰቦች/ድርጅቶች በምድቡ በተቀመጠው ቁጥርና ዓይነት ልክ በራሳቸው ወጭ በመካፈል የሚያነሱ ይሆናሉ።
9. ተጫራቾች በታሸገ ፖስታቸዉ ላይ ስም፣ ፊርማና ስልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸዉ።
10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 45 46 41 21/ 011 558 2432 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. አድራሻ፡ ባህርዳር ቀበሌ 13 ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢሮ (ጎን) በስተምዕራብ በኩል ይገኛል።
Tender details
- Deadline: 2026-05-13
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስረኛው ተከታታይ የሥራ ቀን በ4፡00 ስዓት
- Bid opening: 2026-05-13 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስረኛው ተከታታይ የሥራ ቀን በ4፡30 ስዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: አመልድ ኢትዮጵያ
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: May 03, 2026
- Posted at: 2026-05-04T09:58:46.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.