የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

1.የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ጨረታ ቁጥር 010/2025/26

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ማለትም

  • ተሽከርካሪ የመካኒካል መለዋወጫዎች፣
  • ተሽከርካሪ የኤሌክትሪካል መለዋወጫዎች፣
  • የሞተር ሳይክል መለዋወጫዎች፣
  • የሞተር ሳይክል ከመነዳሪዎች፣
  • የተለያዩ ያገለገሉ የአይቲ ዕቃዎች፣
  • የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች እና የአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
  1. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 11 ቀን 2018 ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ብቻ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራች ያገለገሉ ንብረቶችን ከሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ያገለገሉ ንብረቶችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትይዩ ባለው አስፓልት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ ብራሌ ጥጥ መዳመጫ ግቢ ውስጥ እና የተሽከርካሪና የሞተር ሳይክል መለዋወጫ የሚገኘው ቃሊቲ ከመንገድ ትራንስፖርት የማሽከርከር ብቃት ማረጋገጫ እና ማሰልጠኛ ተቋም አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ /የቀድሞው አማልጋ ሜትድ/ ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በመገኘት ማየት ይችላል።
  3. የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል።
  4. ተጫራች ለንብረቱ የሚሰጠውን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ያስገባል።
  5. የአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ ማሽኖች፣ የአይቲና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን ለመጫረት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን የማስወገድ ወይም መልሶ ለመጠቀም ከኢፌድሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፈቃድ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡
  6. ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2ኛ በግልጽ ይከፈታል።
  7. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሲፒኦ አሸናፊ ለሚሆነው በሚገዛው ንብረት ክፍያ ላይ የሚታሰብ ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-05-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-05-21 10:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Commercial Bank of Ethiopia
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 03, 2026
  • Posted at: 2026-05-06T05:25:37.000Z
  • Buyer website: https://www.combanketh.com

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders