የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መኪና በአንደኛ ደረጃ በግልጽ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ማስታወቂያ

በአ/ከሳሽ እነ ተገኝ በዛብህ በአፈ/ተከሳሽ አቶ በሪሁን ረብሶ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ ፍ/ቤቱ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት አፈ/ተከሳሽ እንደ ፍርዱ ሊፈፅሙ ባለመቻላቸው ምክኒያት በአዲስ አበባ ከተማ የሰሌዳ ቁጥር ኢት 03-A01114 የሆነ የደረቅ ጭንት ተሽከርካሪ መኪና በመነሻ ዋጋ 1,264,868.55/ አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ስልሳ አራት ሽህ ስምንት መቶ ስልሳ ስምንት ብር ከሃምሳ አምስት ሳንቲም/ በሆነ መነሻ ዋጋ በአንደኛ ደረጃ በግልጽ ጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዞል።

1. የሰሌዳ ቁጥር......ኢት 03‐A01114

2. የተሽከርካሪው አይነት ............. ደረቅ ጭንት ተሽከርካሪ መኪና

3. የተሰራበት ሀገር ...........ጣሊያን አይቫኮ

4. የተሽከርካሪው ሞዴል ...380E31H

5. የተሰራበት ዘመን .......2002

6. የሻንሲ ቁጥር…………WJME3TNS00C099868

7. የሞተር ቁጥር .......821022V*825-580614

8. ቀለም..................................ነጭ

9. የነዳጅ አይነት ......ናፍታ

10. የሞተር የፈረስ ጉልበት ...370

11. የተሸከርካሪ ጠቅላላ ክብደት ...28000

12. ነጠላ ክብደት..............12300

13. የጭነት መጠን....... አንድ ሰው እና 156 ኩንታል

14. የሞተር ችሎታ -ሲሲ.... 13798

15. የስሊንደር ብዛት..............6

16. የስራ ፀባይ.........................የግል ንግድ አልግሎት

17. የአክስል ብዛት (ፊት-ኃላ)...... 1-2

18. እንዲከፈል የተወሰነው የብር መጠን 1,243,809/አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ አርባ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠኝ ብር/

በመሆኑም ከላይ የተገለፀውን ተሽከርካሪ መኪና መጫርት ወይም መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች መኪናውን በአካል በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አማካኝነት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ወጣት ማዕከል ያሬድ ሜዳ ፓርኪንግ ውስጥ በማየት መጫረት የሚፈልግ ሁሉ በጎንደር ከተማ ማዕ/ጎን/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 ስዓት እስከ 6፡00 ስዓት በመቅረብ እንድትጫረቱ እያዘዝን ተጫራቾች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን እንድታሟሉ እየገለፅን፡-

1. ተወዳዳሪዎች በተጠቀሰው ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ መኪናው ካለበት ቦታ ለማየት መቅረብ ይጠበቅባቹሃል።

2. ገዥ ሲያሸንፍ አንድ አራተኛውን ወዲያውኑ ያሲዛል።

3. ገዥ ሲያሸንፍ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃሎ ከከፈለ ንብረቱ በስሙ ወዲያውኑ እንዲዛወርለት ይደረጋል።

4. የጨረታ ተወዳደሪዎች በጨረታ ወቅት መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. በጨረታ የሚወዳደሩ እራሳቸው ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የሆናሉ።

6. በጨረታ ወቅት ሁከት የሚፈጥር በሕግ ይጠየቃል።

7. ስመ-ንብረት ማዘወሪያ በጨረታ አሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል።

8. ጨረታው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሃራጅ ባይ የሚመራ ይሆናል ።

ከዚህ በላይ በዝርዝር የቀረበው የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ አሟልታቹህ ለመወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ መኪናው ከሚገኝበት በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አማካኝነት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ወጣት ማዕከል ያሬድ ሜዳ ፓርኪንግ ውስጥ ድረስ በማየት ጨረታው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ እንደሚካሄድ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይገልፃል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-03
  • Publishing entity: Central Gonder Zone High Court
  • Published: May 03, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders