ዳሸን ባንክ አ.ማ አውቶሞቢል ባለበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
የሐራጅ ቁጥር ዳባ/00016/2026
ዳሸን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 1147/11 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚከተለውን የተበዳሪ ወይም አስያዥ ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
የአስያዥ ስም |
የተሽከርካሪው መግለጫ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ጨረታው የሚካሄድበት |
|||||||
|
ዓይነት |
የሠሌዳ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
የተሰራበት ዘመን |
ቀን |
ሰዓት |
ቦታ |
ቀረጥ |
|||||
|
1 |
ፊሮሚ አደም አሳበል |
አዳማ ራስ |
መሀመድ አሚን መሀመድ አውል |
አውቶሞቢል |
አ.አ 02-C16243 |
2ZRY842926 |
RKLKAAAG7 N0506104 |
2021 |
7,100,000 |
ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:00-6:00 |
ቃሊቲ ሸዋ ዳቦ ጀርባ በሚገኘዉ የባንኩ ተሸከርካሪ ማቆሚያ |
ከፍሏል |
ማሳሰቢያ
1. ተጫራቾች የጨረታዉን መነሻ ዋጋ 25% የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) በዳሽን ባንክ ስም በማዘጋጀት በጨረታው ዕለት ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።
2. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት ቃሊቲ ሸዋ ዳቦ ጀርባ በሚገኘዉ የባንኩ ተሽከካሪ ማቆሚያ ቦታ ይካሄዳል።
3. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ሌሎች ግብሮችና እና ሌላ ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ወጪዎችን ይከፍላል።
4. የጨረታው አሸናፊ ደብዳቤ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል:: ባይከፍል ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሀራጅ ሲቀርብ ለሚታየዉ የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል:: በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያሲያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
5. በጨረታው ላይ አስያዥና ተበዳሪ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ፤ ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል።
6. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሠዓት 10 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል።
7. ጨረታው ተጀምሮ በተቀመጠው ሰዓት ውስጥ ካልተጠናቀቀ ሊራዘም ይችላል።
8. ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች የጨረታዉ አሸናፊ ነዉ የሚባለዉ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በፅሁፍ ከባንኩ ሲደርሰዉ ብቻ ነዉ።
9. ባንኩ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-70-45-49 ወይም 0111-70-40-38 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
ዳሸን ባንክ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-05-20
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-05-20 12:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Dashen Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: May 03, 2026
- Posted at: 2026-05-06T07:30:53.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.