የደቡብ ኢትዮዽያ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የሚገለገልባቸውን መኪናዎች ለአንድ አመት በሚቆይ ኮንትራት በሳውላ ከተማ እና አካባቢው ወይም በወላይታ ሶዶ ከተማ ለማስጠገን ይፈልጋል

Description

የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ ጨረታ

የደቡብ ኢትዮዽያ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የሚገለገልባቸውን መኪናዎች ለአንድ አመት በሚቆይ ኮንትራት በሳውላ ከተማ እና አካባቢው ወይም በወላይታ ሶዶ ከተማ ለማስጠገን ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. በትራንስፖርት ሚኒስቴር ወይም በኢት/ክ/መ/ትራንስፖርት ቢሮ ወይም ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00/ሃያ አምስት ሺህ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ CPO/ ሲፒኦ/ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው።
  5. የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ ከመ/ቤቱ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባር ቀርበው ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጥገና አገልግሎት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ በማካተት ኦርጅናል እና ኮፒውን የፋይናሻል እና ቴክኒካል ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ ኢንቨሎፕ በሰም በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ተካታታይ ቀን 8፡30 ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ግዥ ፋይንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባር በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  7. የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8፡45 ሰዓት ላይ ይታሸግና በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።
  8. ተጫራቾች በቂና ምቹ የጥገና መስጫ ቦታ ያላቸው መሆኑን ለጨረታ ኮሚቴዎች ማሳየት ይኖርባቸዋል።
  9. መ/ቤቱ የጥገና አገልግሎት ማግኘት የሚፈልገው በሳውላ ወይም በወላይታ ሶዶ ከተማ ብቻ ነው።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 09 31 56 13 47/ 09 13 30 49 79 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ሳውላ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት

ፍትህ ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-20
  • Publishing entity: Southern Ethiopia Regional Government Justice Bureau
  • Bid bond: 25,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published: May 05, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders