የቤ/ጉ/ክ/መ/አሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ የሠራተኞች ደንብ ልብስ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የቤ/ጉ/ክ/መ/አሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ የሠራተኞች ደንብ ልብስ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
ተጫራቾች በዘርፉ የሥራ መስክ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ እና ከዕዳ ነፃ ስለመሆናቸው ከሚመለከተው አካል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የያዘ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ ፕላንና ል/ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ የዕቃው ዝርዝር መግለጫ እና የዋጋ መሙያ ሰነድ በመውስድ መወዳደር ይችላሉ፡፡
1.የመንግሥት ግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የደንብ ልብሱን በራሳቸው ትራንስፖርት መ/ቤታችን ግቢ ማድረስ የሚችሉ።
3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል እንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዱን ለየብቻ በማሸግ እና በጥቅል ከአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለበት።
4. ተጫራቾች እያንዳንዱ በሰም ታሽጎ ማህተም በመምታት ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እና በመፈረም ኦርጅናል እና ኮፒ የሚል ጽሑፍ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርባት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት አዲስ አበባ ፕላን የስብሰባ አዳራሽ ክፍል ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የማስረከቢያ (የእቃ ርክክብ የሚደረገው)በአሶሳ ከተማ ክልል ገ/ኢ/ጽ/ቤ/ት መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የመጫረቻ ማስከበሪያ ከከፈቱ በፊት ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በባንክ የተረጋገጠ 50,000.00 ሃምሳ ሺህ ብር/ በሲፒኦ ገቢ ማድረግ አለባቸው። የጨረታ መመዝገቢያ እና መክፈቻ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚህ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻችበተገኙበት አዲስ አበባ ፕላን ሚኒስቴር አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም ግን የጨረታ የመከፈቻ ቀን በበዓላት ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይሆናል። ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ሳምፕል ወይም ናሙና በተጠየቀው መስፈርት መሰረት ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው። የዕቃዎች ሳምፕል ናሙና ተጫራቾች በተጠየቀው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ካላቀረባችሁ ጨረታው ውድቅ የሚደረግ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0940749780 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በአሶሳ ዞን የኩርሙክ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-16
- Publishing entity: Kurmuk Woreda FDBE Bureau
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 05, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.