External audit and assurance

ሂኮ ሆራ ቻሪቴብል ኦርጋናይዜሽን /Hiko Hora Charitable Organization/ የ2025 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሂሳብ እንቅስቃሴ በውጪ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል

Description

የኦዲት ሥራ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሂኮ ሆራ ቻሪቴብል ኦርጋናይዜሽን /Hiko Hora Charitable Organization/ በፌዴራል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በምዝገባ ቁጥር 7566 ተመዝግቦ በመስራት ላይ የሚገኝ ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ የ2025 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሂሳብ እንቅስቃሴ በውጪ ኦዲተር ለማስመርመር ስለሚፈልግ፤ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታማሉ

የኦዲት ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤

መስፈርቶቹም፡-

ሀ. የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፡፡

ለ የሙያ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት፡፡

ሐ. የኦዲት የሥራ ልምድ፡፡

መ. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/TIN/

ሲሆኑ አመልካቾች ሥራውን ለመስራት ኦዲት የሚያደርጉበትን ዋጋና ሥራውን አጠናቀው የሚያስረክቡበትን ቀን በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ አስፈላጊውን ማስረጃ በማቅረብ መመዝገብና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር አዲስ፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 0911 91 40 17 /0933848800

ኢ-ሜይል [email protected]

ሂኮ ሆራ ቻሪቴብል ኦርጋናይዜሽን

/Hiko Hora Charitable Organization/


Tender details

  • Deadline: 2026-05-12
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-05-12 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hiko Hora Charitable Organization
  • Published on: Addis Zemen (May 05, 2026)
  • Posted at: 2026-05-06T10:45:48.000Z
← Back to all tenders