የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የተለያዩ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 33/2018
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፋይናንስ ቢሮ በክልሉ ውስጥ የሚገኙትን
- ያገለገሉ ትናንሽ የመስክ መኪናዎች ያገለገሉ ደረቅና የሰው ከባድ መኪናዎች የተቃጠሉ መኪናዎች፤
- ያገለገለ ካት ግሌደር መኪና ያገለገለ ቦምንክ ሩሎ መኪና ያገለገለ ኒው ሆላንድ ትራክተር እስከ ተሳቢው ያገለገለ ዶዘር
- ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች
- የመኪና መለዋወጫና
- የተለያዩ አይነት ያላቸው ብረታብረቶች ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ጀኔሬተሮች
- የመኪና ባትሪዎች
- ለተለያዩ አገልግሎት የሚዉሉ ባህርዛፎች፣ የጽድ ዛፎች እና፤ የግራር ዛፎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ላገለገሉ ተሽከርካሪዎች ምድብ አንድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ላገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫና ቁርጥራጭ ብረታብረቶች፣ ጀኔሬተሮች፣ የመኪና ባትሪዎች፣ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ባህርዛፎች፣ የጽድ ዛፎች እና፤ ለግራር ዛፎች እንደየ ምድባቸው የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በቤ/ጉ/ከ/መ/ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 30 በመቅረብ ሰነዶችን መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ/ ለሚወዳደሩበት ንብረቶች የሚጫረቱበትን የገንዘብ መጠን የጠቅላላ ዋጋ 20% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ በቤ/ጉ/ክ/መ/ፋይናንስ ቢሮ ስም የተሰራ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ቢሮ አዳራሽ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ሠዓት ይከፈታል።
- 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው የሚከፈተው ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- ከጨረታው ጋር በተያያዘ አለመግባባት ቢፈጠር ጉዳዩ የሚፈታው በክልሉ ውስጥ ሆኖ በክልሉ ህገ መንግስት ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በሞባይል ቁጥር 09 10 93 27 74 በመደወል መረዳት ይችላሉ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-05-22
- Publishing entity: Benshangul Gumuz Regional State Bureau of Finance
- Bid bond: 20%
- Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published: May 05, 2026
Documents
Categories
Other SalesSales, Disposals and ForeclosureDisposal SaleVehicle and Machinery ForeclosureVehicle and Machinery SaleTri Wheeler, Motorcycles and Bicycles PurchaseFirewoodEnergy, Power and ElectricityWood and Wood WorkingMachinery and EquipmentAgriculture and FarmingSpare Parts and Car Decoration MaterialsEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesGeneratorsSteel Raw Materials and ProductsSteel, Metals and AluminiumOther MetalsProducts and ServicesAmharic2merkatoBenshangul Gumuz Regional State Bureau of FinanceBeneshangul Gumuz
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.