የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የዎርክ ሾፕ መሣሪያዎች እና የተለያዩ መኪናዎች መለዋወጫ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ከታች ቀጥሎ በሎት አንድ እና በሎት ሁለት የተዘረዘሩትን የዎርክ ሾፕ መሣሪያዎች እና የተለያዩ መኪናዎች መለዋወጫ እቃዎችን ለመግዛት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግ.ሥ.ኮ./ብግጨ/12/2018
|
ተ.ቁ |
የሎት ቁጥር |
የጨረታ አይነት |
የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ (የማይመለስ) በብር |
የጨረታ ማስከበሪያ በብር |
የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
||
|
የመዝጊያ ቀን |
የመዝጊያ ሰዓት |
የመክፈቻ ሰዓት |
|||||
|
1 |
ሎት አንድ |
የጥገና ዎርክ ሾፕ መሣሪያዎች ግዥ |
200 |
100ሺህ |
ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም |
4፡00 |
4:30 |
|
2 |
ሎት ሁለት |
የተለያዩ መኪናዎች የመለዋወጫ እቃዎች ግዥ |
200 |
100ሺህ |
ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም |
8፡00 |
8:30 |
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ በዝርዝር እንድተገለፀው እና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሰረት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች -
1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፤ ቲን ቫት፤ በGP/PPA የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባችሁ እንዲሁም ከገቢዎች ሚ/ር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አ.ማ. አጠገብ የቀድሞው እርሻ መሣሪያዎችና ቴክኒክ አገልግሎት አ.ማ. ግቢ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከላይ በእያንዳንዱ ሎት በተገለፀው ብር መሰረት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ በግልጽ የሚታይና ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን ይኖርበታል።
3. ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና (ለ60 ቀናት የሚቆይ) ማስከበሪያ ከላይ በተገለፀው መሰረት በሲ.ፒ.ኦ. ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋስትናው ለብቻው በአንድ ፖስታ ውስጥ ተደርጎ ከኦርጂናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የጸና ይሆናል።
4. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ዶክመንት መሰረት እያንዳንዱ ሎት-1 እና በሎት-2 ለየብቻ በማድረግ ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሽያል በተለያዩ ፖስታ በማድረግ ፋይናንሽያል ሰነዱ ዋና እና ኮፒ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ በተገለፀው መሰረት ሁኖ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የቴክኒካል ጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል።
6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ስልክ ቁጥር፡-+251 911 984 467 / +251 913 217 657
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
አዲስ አበባ
Tender details
- Deadline: 2026-05-15
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-05-15 14:30
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Agricultural Business Corporation
- Buyer address: ከሳሪስ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
- Bid bond: 100,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published: May 05, 2026
- Posted at: 2026-05-06T12:38:14.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.