ሉሲ ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን በአደጋ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች እና ልዩ ልዩ ቅሪቶች ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 4/2018
ሉሲ ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን በአደጋ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች እና ልዩ ልዩ ቅሪቶች ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ልዩ ልዩ ቅሪቶችን አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቃሊቲ መናኸሪያ ገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ንብረት ማከማቻ ግቢ ውስጥ ከግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሥራ ሰዓት በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ ለዚሁ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ 22 ካፒታል ሆቴል ፊት ለፊት ከዋሪት ሙሉ ጥላ ኢንተርናሽናል ኩባንያ አጠገብ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ የሚገኝ ሲሆን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱት መነሻውን ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ከ1,000.00 ብር ያላነሰ በሉሲ ኢንሹራንስ (አ.ማ) ወይም በእንግሊዝኛ LUCY INSURANCE (SC) ስም ልዩ ልዩ ቅሪቶች የጨረታ ወይም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 5፡30 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:30 ሰዓት አድራሻው ከላይ በተጠቀሰው ዋና መ/ቤት የባንክ ከፍያ ማዘዣውን (CPO) በማቅረብ በመጫረቻው ቅጽ ላይ የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ የሪከቨሪ ዋና ክፍል ይከፈታል።
- አሸናፊ ተጫራቾች በአሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊ ተጫራቾች የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ከሚገዙበት ዋጋ ጋር ይታሰብላቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታውን ያሸነፉበትን ሙሉ ክፍያ አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ዕለት ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ንብረቱን ካልተረከቡ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል።
- አሸናፊ ተጫራቾች በጨረታ የገዙትን ንብረት ጨረታው በተከፈተ በ 7 ቀናት ውስጥ ከኩባንያው ግቢ ካላወጡ ለ10 ቀናት በቀን ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) የምናስከፍል ሲሆን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ካላነሱ በሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ።
- ለጨረታ በቀረቡት ንብረቶች ላይ የሚፈለግ ማንኛውም ዓይነት ወጪዎችን የጨረታ አሸናፊው ይከፍላል።
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው።
- ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114704981/0911634013/0913014519 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ።
Tender details
- Deadline: 2026-05-22
- Bid closing time: 16:30
- Bid opening: 2026-05-23 09:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Lucy Insurance S.C.
- Bid bond: 10% (አስር በመቶ) ከ1,000.00 ብር ያላነሰ
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: May 10, 2026
- Posted at: 2026-05-11T13:03:02.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.