በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ንብረትነታቸው የቅ/ጽ/ቤቱ የሆኑ ያገለገሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ጎማዎች ባሉበት ሁኔታና በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገሉ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች እና ተሸከርካሪ ጎማ
ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ECC‐JBO/02/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ንብረትነታቸው የቅ/ጽ/ቤቱ የሆኑ
- ያገለገሉ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ጎማዎች ባሉበት ሁኔታና በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው በጨረታዉ መወዳደር ይችላሉ።
- በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
- ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዕቃዎችን በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ተገኝተዉ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሚገዙት ዕቃዎች የጨረታ የመሸጫ መነሻ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በሚዘጋበት ቀን እስከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ጠቅላላ የሎት ዋጋ እና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን መስፈርቶች አሟልቶ መገኘት ነው።
- የሎት የመሸጫ የመነሻ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች መስፈርቶችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
- የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲ.ፒ.ኢ.ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚዘጋና የሚከፈት ሲሆን ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዉል መፈረም እና ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል።
- ቅ/ፅ/ቤቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በሥሙ ወይም በሕጋዊ ተወካዩ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በከፈሉ በ10 ቀናት ውስጥ ንብረቶቹን የማንሳት ግዴታ ያለባቸዉ ሲሆን ይህ መሆን ካልቻለ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል፡፡ ዕቃውም በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0915748790 ወይም 0913220473 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን መቀበል ወይም አለመቀበል የሚችል ሲሆን በማነኛውም ጊዜ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን፡-ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 05
ለተጨማሪ መረጃ ፡-በስልክ ቁጥር 0915748790 ወይም 0913220473
በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-26
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 12, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.