በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የተለያዩ ያገለገሉ ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ፣

የጨረታ ቁጥር ኢመአ ሶዶ ዲስትሪክት 02/2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የተለያዩ ያገለገሉ ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በመንግስት የግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ብቁ ተጫራቾች እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች በድርጅት ሥም ወይም በግለሰብ ደረጃም መጫረት የሚቻል ሲሆን በድርጅትም ይሁን በግለሰብ ደረጃ መግዛት ይቻላል።

2. ተጫራች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ በመ/ቤታችን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000322276919 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ወላይታ ሶዶ ከነዳጅ ዲፖ አለፍ ብሎ ጎፋ ማዞሪያ አከባቢ ባለው ቢሮ በመምጣት ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ከሰኞ-ዓርብ የጨረታ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው

4. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ታሽጎ ከቀኑ 9፡20 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 046-551-1292 መደወል ይችላሉ።

6. የንብረቶቹ ዝርዝር መነሻ ዋጋ የተቀመጠ ቢሆንም አሸናፊ መሆን የሚችለው በጥቅል ወይም በድምር ከፍተኛ ዋጋ ባቀረበው ነው።

7. ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት በኋላ ባሉት 7 የሥራ ትናት ገንዘቡን ከላይ በተገለፀው ሂሳብ ቁጥር ገቢ ማድረግ አለበት።

8. አሸናፊው ገንዘቡን ገቢ ካደረገ በኋላ ባሉት ተከታታይ ሥራ ጥናት ንብረቱን ሙሉ በሙሉ መረከብ አለበት።

9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ

ስልክ ቁጥር 046 551 1292

ፖ.ሳ.ቁጥር 116

አድራሻ፡ ወላይታ ሶዶ ከነዳጅ ዲፖ አለፍ ብሎ ጎፋ ማዞሪያ

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-26
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00
  • Bid opening: 2026-05-26 15:20
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡20
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Ethiopian Roads Administration (ERA)
  • Buyer address: ወላይታ ሶዶ ከነዳጅ ዲፖ አለፍ ብሎ ጎፋ ማዞሪያ
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 12, 2026
  • Posted at: 2026-05-12T11:32:08.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders