እፎይታ በኮልፌ ገበያ ማዕከል አ/ማ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው መድኃኔዓለም መሰናዶ ት/ቤት አካባቢ በ 668 ካሬ ባረፈ ይዞታ ላይ ሊገነባ ላቀደው ቅይጥ ህንፃ አጠቃላይ የዲዛይን ሥራ በጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ ደረጃ 2 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የዲዛይን ሥራ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር እ/በ/ገ/ማ/001/2018

እፎይታ በኮልፌ ገበያ ማዕከል አ/ማ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው መድኃኔዓለም መሰናዶ ት/ቤት አካባቢ በ 668 ካሬ ባረፈ ይዞታ ላይ ሊገነባ ላቀደው ቅይጥ ህንፃ አጠቃላይ የዲዛይን ሥራ በጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ ደረጃ 2 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል።

በመሆኑም

1. የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡

2. ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው

3. የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (Supplier list)፣

4. ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።

5. ተጫራቾች ላለፍት አምስት ዓመታት ቢያንስ 3 ደረጃቸዉን የጠበቁ ተቀራራቢ ዲዛይኖችንና አጠቃላይ የበጀት መጠኑ ከ1.5 ሚልየን ብር በላይ የሆነ ኮንትራት ተፈራርመዉ ባግባቡ ያስረከቡ ሊሆን ይገባል።

6. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር/10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በእፎይታ በኮልፌ ገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች የማይመለስ ቅጂ(Copy) ይዞ በመቅረብ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond Or Bid Security) በባንክ ትእዘዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ለብር 50,000.00 በእፎይታ በኮልፌ ገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ስም ማስያዝ አለባቸው።

8. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ በጨረታው TOR በተገለፀው መሰረት ለቴክኒካል ና ለፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ በድምሩ አራት ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም በሰም የታሸገውን 4 ፖስታ የቴከኒካል ሰነድ ሁለቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በሰም በማሸግ እና የፋይናንሻል ሰነድ ሁለቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በሰም በማሸግ እና ሁለቱን ፖስታና የCPO ፖስታውን በአንድ እናት ፖስታ በሰም በማሸግ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው ቀንናሰዓት ድረስ ብቻ በእፎይታ በኮልፌ ገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው በአሥራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በእፎይታ በኮልፌ ገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲገኙ የተጋበዙ ሆኖ ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።

10. ለበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በአክሲዮን ማህበሩ ፅ/ቤት ኮልፌ አጠና ተራ በእፎይታ በኮልፌ ገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 30 54 04 99 መረዳት ይቻላል።

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

እፎይታ በኮልፌ ገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-05-22
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር/10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-23 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአሥራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Efoyta Bekolfe Market Center Share Company
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: May 13, 2026
  • Posted at: 2026-05-13T09:39:39.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders