በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት የሚኙትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር DCDF 010/2018
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት የሚኙትን ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ መወዳደር ይቻላል።
- ተጫራቾች የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ፋይናንስ ዴስክ በመምጣት የተሽከርካሪዎች ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው ከግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም ባሱት የስራ ቀናቶች ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ከሰዓት 7፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ መገዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም ባሉት የስራ ቀናቶች ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:30-6፡30 ከሰዓት 7:30-11፡00 ሰዓት ተሸከርካሪዎቹን በአካል ማየት የሚችሉ ሲሆን ተሸከርካሪዎቹን ለማየት ሲመጡ የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ አስተዳደርና ፋይናንስ ቡድን 4ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉለውም።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ 20 በመቶ (20%) በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defense Construction Design Enterprise) ስም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) ብቻ ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመታሸጉ በፊት በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ሲፒኦ(CPO) የተሰራጩ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች የግምገማው ውጤት ለተጫራቾች ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በ20 የስራ ቀናቶች ውስጥ ሲፒኦ(CPO) ተመላሽ ይደረጋል።
- ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል.
- የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተወዳዳሪ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።
- በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን ብቻ በመሆናቸው የኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘብ በሻጭ እና በገዥ መካከል ተግባራዊ ይደረጋል.
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 0633/ 011 896 0623
አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት
የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ
Tender details
- Deadline: 2026-05-22
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-05-22 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defence Construction Design Enterprise
- Buyer address: ወሎ ሰፈር አምባሰል ህንፃ ፊት ለፊት የቀድሞው ኖሬላ ግቢ ውስጥ
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: May 13, 2026
- Posted at: 2026-05-13T11:03:44.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.