አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የሀይል መጠባበቂያ እና መቆጣጠሪያ ባትሪ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የሀይል መጠባበቂያ እና መቆጣጠሪያ ባትሪ ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ የክልሉን ህዝብና ሰማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት በማንቀሳቀስ በትምህርት በጤና እና በስራ እድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ ማህበራዊ ተጠቃሚነት አስተዎጾኦ በማድረግ ተልእኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው። በመሆኑም ማህበሩ ብቁ እና መስፈርቱን የሚያሟሉ አቅራቢዎች (Eligible and qualified Suppliers to Submit bids for the Supply, Delivery, and Warranty Support of Six /6/ Lead-Acid Batteries to be used for power Backup Applications) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁም መሰረት

1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIn no ያላቸው

2. የግዥ መጠን 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

3. በመንግስት ግዥ በአዲሱ አቅራቢዎች ዝርዝር መረጃ ላይ ማለት(https://www.egp.ppa.gov.et ) መመዝገባቸውን የሚችሉ

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመስከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አስባቸው።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማያመስስ 500 /አምስት መቶ ብር / በመክፈል አዲስ አበባ በሚገኘው አልማ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 203 ማግኘት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ዋስትና ማስያዝ አስባቸው፤

7. የሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል።

8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዶክመንት ላይ ያስምንም ስርዝ ድልዝ በመሙላት አንድ ወጥ በሆነ ኢንቨሎፕ ማስገባት አስባቸው፤

9. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት አዲስ አበባ አልማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 203 መግዛት የሚቻል ሲሆን ፤የጨረታው ማወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናስና ፎቶ ኮፒ የፋይናንስ ስብቻ የቴክኒክ ስብቻ በማያያዝ በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካስሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አዲስ አበባ ቦሌ ማተሚያ ቤት ጎን አልማ ህንፃ 2ኛ ቢሮ ቁጥር 203 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011 551 2528 /በመደወል ማግኘት ይችላሉ።


Tender details

  • Deadline: 2026-05-22
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-22 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: አማራ ልማት ማህበር ማ/ጽ/ቤት
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 500 /አምስት መቶ ብር /
  • Published: May 13, 2026
  • Posted at: 2026-05-13T11:27:45.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders