ቴክኖስታይል ኃላ.የተ.የግል ማህበር ያገለገሉ የተለያዩ ቀላል ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ቴክኖስታይል ኃላ.የተ.የግል ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ጠ/አ/02/2018

ቴክኖስታይል ኃላ.የተ.የግል ማህበር ያገለገሉ የተለያዩ ቀላል፤ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም፡

1. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታዉን ሠነድ ማስታወቂያዉ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00፤ ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 11፡00 ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ ጥዋት ከ2፡30 -- 6፡00 ብቻ የማይመለስ 100(መቶ) ብር በመክፈል ካዛንቺስ እናት ባንክ አጠገብ ባለዉ ዋና መስሪያ ቤት፤ቃሊቲ ማሰልጠኛ አጠገብ ባለዉ ፋብሪካ እና ለገጣፎ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ መዉሰድ ይቻላል።

2. ማንኛዉም ተጫራች ለሚጫረተዉ ለእያንዳነዱ ተሸከርካሪ በገባዉ የጨረታ ሰነድ ላይ ባስገባዉ የጨረታ መነሻ ዋጋ መሠረት ያስገባዉ ዋጋ 20% በባንክ የተመሰከረለት CPO በጨረታዉ መክፈቻ ሰዓት ጨረታዉ ከመጀመሩ በፊት ማስያዝ የሚኖርበት ሲሆን ጨረታ ማስከበሪያዉ ለተሸነፈ ተጫራች ወዲያዉኑ የሚመለስ ሲሆን የአሸናፊ ተጫራች ሙሉ ክፍያዉን ሲከፍል የሚታሰብ /የሚመለስ ይሆናል።

3. ጨረታዉ አርብ ግንቦት 21/2018 (May 29/2026) ከሠዓት በኋላ 8፡30 ተዘግቶ ከቀኑ 9፡00 በካዛንቺስ በሚገኘዉ ዋና መስሪያ ቤት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ተወካዮቻቸዉ በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።

4. በጨረታዉ ያሸነፈ ማንኛዉም ተጫራች ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10(አስር) ቀን ቀናት ዉስጥ ለተቋሙ ገቢ ማድረግ ያለበት ሲሆን ይንን ያላደረገ ተጫራች ያስያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለተቋሙ ገቢ ሆኖ ተሸከርካሪዉ ለዳግም ጨረታ ይቀርባል።

5. በጨረታዉ ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ተሸከርካሪ ሙሉ ክፍያ ከፈጸመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናቶች ዉስጥ ሙሉ በሙሉ ተሸከርካሪዉን የማንሳት ግዴታ ያለበት ሲሆን በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ተሸከርካሪዉን ለማንሳት ያልቻለ የጨረታ አሸናፊ የተሰጠዉ የጊዜ ገደብ ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ ለእያንዳነዱ ተሸከርካሪ በቀን ብር 200 (ሁለት መቶ) የማቆያ ኪራይ የመክፈል ግዴታ አለበት።

6. ተሽከርካሪዎቹ የሚፈለግባቸዉን ማንኛዉንም ቀረጥና ዉዝፍ ዕዳ ቢኖር ተቋሙ ይሸፍናል። ነገር ግን የስም ማዛወሪያ እና የቦሎ ክፍያ በገዢዉ በኩል ይሸፈናል።

7. ተጨማሪ ዝርዝር የሽያጭ ሁኔታ እና የጨረታ መመሪያ በሚሸጠዉ የጨረታ ሠነድ ላይ በግልጽ ይቀመጣል።

8. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 670-4451 ለገጣፎ 09 13-25-44-46/ 09 09-55-17-14 ወይንም 09 13-51-79-79 ይደውሉ 

ቴክኖስታይል ኃላ.የተ.የግል ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-05-29
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid opening: 2026-05-29 15:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Techno Style PLC
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ 20%
  • Bid document price: 100 ብር
  • Published: May 13, 2026
  • Posted at: 2026-05-13T11:37:23.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders