የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ቱታ፣ ጋዎን፣ ልዩ ልዩ ዓይነት ጫማዎችና የመፀዳጃ ቤት ወረቀት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ
የግዥ መስያ ቁጥር GN-024/2018 እና GN-025/2018
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ 2017 እና 2018 የበጀት ዓመት ለሠራተኞቹ ማቅረብ የሚገባውን ቱታ፣ጋዎን፤ልዩ ልዩ ዓይነት ጫማዎችና የመፀዳጃ ቤት ወረቀት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዘርፉ የተመዘገበ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያበቃ የታክስ ክሊራንስ የሚያቀርቡ በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና ከዚህ በፊት በነበሩ ጨረታዎች የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃዎችን የሚያቀርቡ በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋናው መ/ቤት እቃ ግዥና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ወይንም የአስተዳደሩ ጎንደር ዲስትሪክት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ። (ከዚህ በፊት በወጣው ጨረታ የጨረታ ሰነድ ገዝተው የነበሩ ድርጅቶች ይህን ሰነድ በአካል ቀርበው በነፃ መውሰድ ይችላሉ)።
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ላሉት 20 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ከ 15ኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ላይ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋናው መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ከላይ የተመለከቱት ሁለቱ የግዥ መለያዎች የተለያዩ ግዥዎች በመሆናቸው ለየብቻ መቅረብ ይገባቸዋል።
የጨረታ ሰነዱ ከሚጠይቀው ሥነ-ሥርዓት ውጭ ተዘጋጅተው የሚቀርቡ የጨረታ ፖስታዎች ውድቅ ሊደረጉ ስለሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥሞና እንዲረዱ እናሳስባለን።
መ/ቤታችን ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ እና ሁኔታ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የመረጃ ስልክ ቁጥር 09 11 66 49 88 መደወል ይቻላል።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-06-03
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ላሉት 20 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ከ 15ኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡15
- Bid opening: 2026-06-03 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ላሉት 20 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ከ 15ኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጎንደር ዲስትሪክት
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 14, 2026
- Posted at: 2026-05-14T07:22:45.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.