ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አ.ማ የተለያዩ ያገለገሉ የህዝብ እና የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በሽያጭ ለማስወገድ ይፈልጋል

Description

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታው ቁጥር [Gada/NCB/10/2018]

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አ.ማ የተለያዩ ያገለገሉ የህዝብ እና የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በሽያጭ ለማስወገድ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች እና የታደሰ የኗሪነት መታወቂያ ያለው ወይም ያላት እና በማንኛውም ንግድ ስራ ላይ

2. ውሩ የተሰማራ ወይም የተሰማራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።

3. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም ወይም በመፈርም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አጠቃላይ ከተወዳደሩበትን ዋጋ 2% በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያየ ፖስታ በማሸግ ሁሉንም ሰነዶች ደግሞ በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።

5. የጨረታ ሰነድ የገዙ ተወዳዳሪውች የገዙትን ሰነድ እና ደረሰኝ በመያዝ ተሽከርካሪዎችን ሞጆ በሚገኘው የድርጅቱ ዎርክ ሾፕ ግቢ ውስጥ ማየት ይቻላል

6. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10 % በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም

8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡

9. የጨረታ መክፈቻ ቀናት፤ ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

አድራሻ:- ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-558-25-19 / 0991 330 694 / 0909 273 110

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-05-29
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-29 14:30
  • Bid opening (note): በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Geda Transport and Logistics S.C.
  • Buyer address: ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 14, 2026
  • Posted at: 2026-05-14T07:55:38.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders