የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የሆነ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ሰነድ ቁጥር PPS/MP-1FB/10/08/2018

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የሆነ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. በጨረታው ላይ የሚወዳደሩት በማዕድን ሚኒስቴር የተለዩ የብረት አቅላጭ የግል ድርጅቶች የሆኑና የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና መታወቂያ ማቅረብ የሚችሉ ናቸው።
  2. ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ በመምጣት የብረቶቹን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ ገቢ በማድረግና ያስገቡበትን የባንክ ስሊፕ ይዘው በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ብረታ ብረቶቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ቁርጥራጭ የብረት ዓይነት የጨረታ መነሻ ጠቅላላ ዋጋውን 2% (ሁለት በመቶ) ነገር ግን ብር 100,000 መቶ ሺ ያልበለጠ ዋስትና ያላስያዘ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው።
  5. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  6. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል። ይሁንና የብረታ ብረቶቹን ጠቅላላ ግምታዊ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ነገር ግን ብር 100,000 አንድ መቶሺ ያልበለጠ ዋስትና ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
  7. የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም።
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ይሁንና ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መከፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ብረታ ብረቶች ሙሎ ከፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን በ10% (አሰር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች ያሸነፉትን ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ የሚዛንና ሌሎች ወጪዎችን በመሸፈን ብረታ ብረቱ ከሚገኝበት ስፍራ ቅርብ በሆነ ፕሪንት አውት ማውጣት በሚችል የመንግስት የምድር ሚዛን በማስመዘን ውል በፈረሙ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቱን በማንሳት ማጠናቀቅ አለባቸው። ግምታዊ መጠኑ ከፕሪንት አውት ከሚገኘው ትክከለኛ የብረቱ መጠን ጋር የሚኖረው ልዩነት ታስቦ አሸናፊው ተጫራች ተጨማሪ ክፍያ የሚኖርበት ከሆነ የውል ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ልዩነት የሚኖረውን ሃሳብ መክፈል ያለበት ሲሆን በትርፍነት የሰጠው ተመላሽ የሚደረግለት ገንዘብ ካለም በአገልግሎቱ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል።
  11. አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
  12. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10(አስር) ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
  13. አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ወይም ሌላ ጨረታውን ለመሰረዝ የሚያበቃ ምከንያት ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ፡- www.pps.gov.et  ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

የፌ ዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-03 10:15
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:15 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ቁርጥራጭ የብረት ዓይነት የጨረታ መነሻ ጠቅላላ ዋጋውን 2% (ሁለት በመቶ) ነገር ግን ብር 100,000 መቶ ሺ ያልበለጠ
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: May 14, 2026
  • Posted at: 2026-05-14T08:06:48.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders