ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ እና የጽዳት መጠበቂያ መሳሪያዎች በድጋሜ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የደንብ ልብስ እና የጽዳት መጠበቂያ መሳሪያዎች ግዝ ግልፅ ጨረታ መመሪያና ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዕ/ደ/ዕ/ት/ድ/አቅ/007/18
ድርጅታችን በ2018 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ እና የጽዳት መጠበቂያ መሳሪያዎች በድጋሜ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ተጫራቾች፡-
1. የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችልና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ፤
2. ተጫራች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ እና የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ በተለያዩ ድርጅቶች የጽዳት መገልገያ መሳሪያዎች እንዲሁም የደንብ ልብስ አቅርቦትስለመፈጸሙ የሚያረጋግጡ ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንስና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይቻላል፤
4. ተጫራቾች ከዚህ የጨረታ ሰነድ ጋር በቀረበው የዕቃ ዝርዝር መሰረት የሚወዳደርበትን ዕቃ ነጠላ ዋጋ (unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total Price) በግልፅ አሃዞች በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት ይህ የጨረታ ጥሪ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በአቅ/ፋ/ማ ዳይክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ በዚሁ የመጨረሻ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የጨረታው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተገለፀው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል፤
5.ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በመሙላት ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኦርጅናል፣ ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኮፒ ፋይናንሽያል ኦርጅናል፣ ፋይናንሽያል ኮፒ በማለት ለይተው በተለያየ ፖስታ በማድረግ፣ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
6. ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ እና ናሙና ከ70% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
7. ተጫራቾች የፋይናንሽያል ሰነድ ከ30% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
8. የቴክኒካል ግምገማ ውጤት 70/100 ወይም 51/70 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ለፋይናንሻል ውድድር ግምገማ ያልፋሉ፡፡ በፋይናንሻል ግምገማ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል፡፡
9. ተጫራቾች በየሎቱ በሠንጠረዥ ላይ የተመለከተውን የጽዳት መገልገያ መሳሪያ እንዲሁም የደንብ ልብስ በመጥቀስ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (CPO) የሚጫረቱበትን የእያንዳንዱ ሎት፤
- ለሎት 1 የደንብ ልብስ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣
- ለሎት 2 የጽዳት መገልገያ መሳሪያዎች ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው፤
10. አሸናፊ ተጫራች ውጤቱ በፅሁፍ እንደተገለፀለት በ7 (ሰባት) የሥራ ቀናት ውስጥ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና (ፐርፎርማንስ ቦንድ) ከጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ በማስያዝ በግንባር ቀርቦ የተዘጋጀውን ውል በመፈረም በ15 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ንብረት ሙሉ አቅርቦት መፈጸም ይኖርበታል፤
11. ተጫራች የጽዳት መገልገያ መሳሪያዎች እንዲሁም የደንብ ልብስ በየሎቱ ናሙና ከዋጋ ከማቅረቢያ ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርበታል፤
12. ድርጅቱ ይህንን ጨረታ ለአሸናፊ በሚሰጥበት ጊዜ የጽዳት መገልገያ መሳሪያዎች እንዲሁም የደንብ ልብስ የመግዣ የነጠላ ዋጋ ሳይቀር ብዛት በ20% የመጨመር/የመቀነስ መብት አለው፤
13. የጨረታ አሸናፊ ውጤት እንደተገለፀ በ05 ቀን ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ/የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና አገልግሎት የሚውል ዋጋ 10 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ CPO በማስያዝ ውል ይፈፅማል፤
14. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡-
- በስልክ ቁጥር 011 4 39 00 75/35 92/15 69/011 439 10 27
- ፋክስ 011 439 63 36/0114 74 71 41 ፖ.ሳ.ቁ. 2562 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ
- አድራሻ፡- ቃሊቲ ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት 70 ሜትር ገባ ብሎ
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-05-25
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ጥሪ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-25 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ጥሪ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Elet Derash Relief Transport Enterprise
- Buyer address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንፃ ጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 15, 2026
- Posted at: 2026-05-15T07:37:09.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.