የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ የሎተሪ ቅስቀሳ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ቲሸርት፣ ኮፍያ እና ባግ ዕቃዎችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መስያ ቁጥር ኢሎአ/09/2018
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ የሎተሪ ቅስቀሳ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ቲሸርት፣ ኮፍያ እና ባግ ዕቃዎችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም በተከፈተ የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000004652782 ገቢ በማድረግ ዋናውን ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ በማሲያዝ ዋናውን ማስረጃ ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች የመጫረቻ ስነዶችን የቴከኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋና እና አንድ ቅጂ ለየብቻው በፖስታ በማድረግና በፅሁፍ በመለየት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ክሊራንስ፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት፣ የማጭበርበር ድርጊት ለለመፈፀም ቃል የሚገባበት ቅፅ ሞልታችሁ ማህተምና ፊርማ አድርጋችሁ የመጫረቻ ሰነዶቻቹሁን አሟልታችሁ በማቅረብና የጨረታ ማስከበሪያውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው:: ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ግንቦት 19 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡ አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011-126-78-16 ደውሎ መረዳት ይቻላል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
Tender details
- Deadline: 2026-05-27
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-05-27 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
- Bid bond: 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: May 15, 2026
- Posted at: 2026-05-15T07:37:12.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.