በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን የተለያዩ ያገለገሉ መስታወት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን የተለያዩ ያገለገሉ መስታወት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከተውን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. በግልጽ ጨረታው በቀረበው ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተለያዩ ያገለገሉ መስታወቶች ባለበት ሁኔታ በማየት መጫረት ይቻላል።

2. በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ፊት ለፊት የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ክፍያና ሂሳብ ቡድን በመምጣት የንብረቱን ዝርዝር መመሪያ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሰነድ በመግዛት ሊመለስ በማይችል ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር /ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቱን ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች በአሃዝ እና በፊደል በሰጠው የዋጋ መሙያ በመሙላት ማስገባት ሲችሉ ልዩነት ካለው ከፍተኛ ዋጋ በመውሰድ ያወዳድራል።

5. ተጫራቾች የሚገዙትን ዕቃዎች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቹዋል።

6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር ተከታታይ የስራ ቀናቶችን ከሰኞ እስከ አርብ ያሉ ቀናቶችን ታሳቢ በማድረግ በ11ኛው ቀን የሰነድ ሽያጭ ተጠናቆ በ11ኛው ቀን ማለትም ጨረታው ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችን ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን ቢሮ ላይ ይከፈታል። ሆኖም የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳደገኝ ቢቀር የጨረታው መከፈት አያስተጓጉልም።

7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ለአሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7/ሰባት/ የስራ ቀናት ውስጥ ቀሪ ክፍያውን በማጠናቀቅ የአሸነፈበትን ንብረት በ5/አምስት/የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርበታል። የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋ እና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለፁትን አማልቶ መገኘት አለበት።

8. የንብረቶቹ የጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) ያስያዘ እና በሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦች ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውደቅ ይደረጋል።

9. አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ለተመደበው ዕቃዎች ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል እና ከጨረታ መነሻ ዋጋ በታች አና መነሻ ዋጋ ሞልቶ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።

10. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርባቸዋል።

11. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸው ንብረቶች ሙሉ ከፍያ ከፍሎ እስከሚወስድ ድረስ ለውል አስተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) በጥሪ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት።

12. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ አጠቃለው በመከፈል ንብረታቸውን በ5/አምስት/ ቀናት ማንሳት ይኖርባቸዋል።

13. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011 827 5923 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

14. መ/ቤቱ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- መድሀኒአለም ከራስ ሃደሉ መዝናኛ ማዕከል አጠገብ አዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ፊት ለፊት

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 401 4ኛ ፎቅ ፊት ለፊት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡደን

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-29
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናቶችን ከሰኞ እስከ አርብ ያሉ ቀናቶችን ታሳቢ በማድረግ በ11ኛው ቀን የሰነድ ሽያጭ ተጠናቆ በ11ኛው ቀን ማለትም ጨረታው ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-29 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናቶችን ከሰኞ እስከ አርብ ያሉ ቀናቶችን ታሳቢ በማድረግ በ11ኛው ቀን የሰነድ ሽያጭ ተጠናቆ በ11ኛው ቀን ማለትም ጨረታው ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ketema Sub City Design and Construction Works Bureau
  • Buyer address: መድሃኒያለም መሰናዶ ት/ቤት አካባቢ ራስ ኃይሉ ስፖርት ማዕከል ጎን በሚኘው የክፍለ ከተማው ህንፃ 4ኛ ፎቅ
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 15, 2026
  • Posted at: 2026-05-15T07:52:47.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders