ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሽሮ ሜዳ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ በማወዳደር ባሉባት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ዕቃዎች የጨረታ ሠነድ
የጨረታ ቁጥር-Service 0005/2018
ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሽሮ ሜዳ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ በማወዳደር ባሉባት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ዕቃዎቹን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሽገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ አዲስ በተገነባው ሕንጻ ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 003 በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
በዚሁ መሠረት፣
1. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎችን ሽሮሜዳ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በአካል ተገኝተው በማየት ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ ከግንቦት 8 ቀን 2018 ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለፀው መ/ቤት አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
2. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ላይ ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ላይ በዋናው መ/ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል።
3. በጨረታው የሚሳተፍ ተጫራች በራሱ ስም የግብር መክፈያ ቁጥር(TIN NO) እና 50.000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሸገር ዳቦና ዱቄት ፋብሪካ ቅጥር ግቢ አዲስ በተገነባው ሕንጻ አራተኛ ፎቅ ይህ ማሰታወቂያ ከግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓም ከቀኑ 8፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ እና የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡-
ሲፒኦ በማንኛውም ባንክ በሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም ማሠራት ይችላሉ፤
ዋጋ ሲያስቀምጡ ስርዝ ድልዝ ወይም በተሰጠው ሠንጠረዥ መሠረት በትክክልና በግልፅ የዋጋ ማቅረቢያ መሠረት ግልፅ መረጃ መስጠት ያለበት ሲሆን ነገር ግን አሻሚ የሆነ ሰነድ ቢገኝ ውድቅ ይሆናል።
ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-05-27
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ከግንቦት 8 ቀን 2018 ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-27 14:30
- Bid opening (note): ከግንቦት 8 ቀን 2018 ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 8:30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Moha Soft Drinks Industry S.C.
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: May 16, 2026
- Posted at: 2026-05-16T07:54:58.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.