ምሥራቅ የምግብ ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማ ልዩ ልዩ ያገለገሉ የጭነት ተሽከርካሪዎችን፣ የኤሌክትሪክ ሞተሮች፣ ባዶ ካርቶኖችን እና የፒፒ ከረጢቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሸያጭ
ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2018
ድርጅታችን ምሥራቅ የምግብ ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማ ልዩ ልዩ ያገለገሉ የጭነት ተሽከርካሪዎችን፣ ባዶ ካርቶኖችን እና የፒፒ ከረጢቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት እነዚህን ዕቃዎች ተጫርቶ መግዛት ይችላል።
- ሎት 1 ያገለገሉ ልዩ ልዩ የጭነት ተሽከርካሪዎች
- ሎት 2 ያገለገሉ ልዩ ልዩ የኤሌክትሪክ ሞተሮች
- ሎት 3 የተለያዩ ባዶ ካርቶኖች እና የፒፒ ከረጢቶች
1.በዚህ ጨረታ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘውትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2 00 እስከ 11፡00 አንዲሁም ቅዳሜ እስከ 6፡00 መውሰድ ይችላሉ።
3. የዕቃዎች ሽያጭ የሚከናወነው ባሉበት ሁኔታ መሠረት ይሆናል ።
4. በሎት 1 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. በሎት 2 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። በሎት 3 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ የያዘ የጨረታ ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በመጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል። 10ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በተከታዩ ቀን ይከፈታል።
7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 53 48 02 00/ 09 07 88 12 91 ወይም ጎተራ ማሳለጫ አካባቢ ያሬድ ቤተክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
ምሥራቅ የምግብ ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማ
Tender details
- Deadline: 2026-05-25
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-05-25 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: East Food Processing Manufacturing P.L.C.
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 16, 2026
- Posted at: 2026-05-16T08:05:49.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.