አቡነ ዜና ማርቆስ የሕፃናትና አረጋውያን መርጃ ማኅበር የሂሳብ መዝገቡን በዓለም አቀፍ የመንግስታዊ ዘርፍ የሂሳብ አያያዝ መስፈርት (IPSAS) መሠረት ተመርምሮ እንዲቀርብ ይፈልጋል
Description
የውጭ ኦዲት አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን አቡነ ዜና ማርቆስ የሕፃናትና አረጋውያን መርጃ ማኅበር የሂሳብ መዝገቡን በዓለም አቀፍ የመንግስታዊ ዘርፍ የሂሳብ አያያዝ መስፈርት (IPSAS) መሠረት ተመርምሮ እንዲቀርብ ይፈልጋል።
በመሆኑም መስፈርቱን የሚያሟሉ የውጭ ኦዲት ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መሠረታዊ መስፈርቶች፡-
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ።
- ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE) የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፡፡
- በIPSAS የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ስልጠና ያላቸውና በዘርፉ በቂ ልምድ ያላቸው።
የሥራው ዝርዝር (Scope of Work)
1. የድርጅቱን የ2026/2019 የዓመተ ምህረት ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት (3) በጀት ዓመት የሂሳብ መዝገብ በIPSAS መሠረት ኦዲት ማድረግ።
2. የኦዲት አስተያየት እና የማኔጅመንት ደብዳቤ (Management Letter) ማቅረብ።
3. ሥራው ተጀምሮ የሚጠናቀቅበትን ግልጽ የጊዜ ሰሌዳ ማሳወቅ።
የመወዳደሪያ ሰነድ አቀራረብ፡-
ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንስ መወዳደሪያ ሃሳባቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ድረስ ብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በሆም ዲፖ ወደ ውስጥ 300 ሜትር ንላ-03-0725 መንገድ በሚገኘው ቢሮአችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
አድራሻ፡- የድርጅቱ ስም፡ አቡነ ዜና ማርቆስ የህጻናትና አረጋዉያን መርጃ ማኅበር
ስልክ ቁጥር፡-0984 040 404 / 0960 116 313
ኢሜይል፡ zenamarokos.abune@gmail.com
ማሳሰቢያ፦ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፣ በስልክ ቁጥር 09 84-04-04-04 / 0960 116 313 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አቡነ ዜና ማርቆስ የሕፃናትና አረጋውያን መርጃ ማኅበር
Tender details
- Deadline: 2026-05-28
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት
- Bid opening: 2026-05-28 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Abune Zena Marqos Children and Elderly Aid Association
- Published: May 17, 2026
- Posted at: 2026-05-18T08:27:14.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.