የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር እና ፕሪንተር ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር EEP/TBP/NCB/12/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ ድስክቶፕ ኮፕፒውተር እና ፕሪንተር ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና በግዥ ኤጀንሲው ድህረ ገጽ (eGP) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
2. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋና መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ትራንስሚሽን ኮንስትራክሽን የሂሳብ ቁጥር 1000252665203 ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር- 19 ምድር ወለል ትራንስሚሽን ቢዝነስ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 114 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከተውን የላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ድስክቶፕ ኮፕፒውተር እና ፕሪንተር ግዥ የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሉፕ የጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/12/2018 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
No |
Description |
የጨረታ ዋስትና/ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
የላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ ድስክቶፕ ኮምፒውተር እና ፕሪንተር ግዥ |
500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር ከ00/100) |
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም.ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡15 ሰዓት |
5. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251 11 67-3219 መደወል ይችላሉ።
6. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
Tender details
- Deadline: 2026-06-01
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-06-01 14:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Electric Power
- Bid bond: 500,000.00 ብር
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published: May 17, 2026
- Posted at: 2026-05-18T08:35:11.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.