የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ኮርፖሬሽናችን ሳሪስ በሚገኘው ግቢ ውስጥ ያሉትን ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፣ ንቃይ ቆርቆሮች እና ቁርጥራጭ የተሽከርካሪና ሌሎች ብረታ ብረቶች ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ኮርፖሬሽናችን ሳሪስ በሚገኘው ግቢ ውስጥ ያሉትን ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፣ ንቃይ ቆርቆሮች እና ቁርጥራጭ የተሽከርካሪና ሌሎች ብረታ ብረቶች ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው።

1. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውንና የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 1000 ብር/አንድ ሺህ/ በመክፈል ከግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ከግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ዘወትር ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ከዋናው መ/ቤት /አዲስ አበባ/ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 3፡00-6፡30 እንዲሁም ከሠዓት ከ7፡30- 11፡30 እና ቅዳሜ ከ3፡00 እስከ 6፡30 ሠዓት መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ከግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ንብረት 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሲሞሉ በግልጽ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ማሳየት አለባቸው።

5. ጨረታው ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

6. የጨረታው አሸናፊ ተጫራች በጨረታው ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያ በ 5 /አምስት/ የሥራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል። በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሳ ከ5ኛው ቀን በኋላ ላላነሳበት ቀን በየቀኑ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ቅጣት የሚከፍል ይሆናል።

7. አሸናፊው በራሱ ወጪ የተለያዩ ብረታ ብረቶች፣ንቃይ ቆርቆሮች እና ቁርጥራጭ የተሽከርካሪና ሌሎች ብረታ ብረቶች ማንሳት፣ ማስጫንና ማጓጓዝ ይኖርበታል፡፡

8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-416-7347/ 011-466 9336 መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፡- በቅሎ ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 011 467-1902/ 011 416-3483 አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-05-22
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-05-22 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Trading Businesses Corporation
  • Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published: May 17, 2026
  • Posted at: 2026-05-18T09:30:47.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders