የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኝውን እርጥብ ቆዳና ከበጎች እና ፍየሎች የሚገኘው እርጥብ ሌጦ፣ የስጋና አጥንት መኖ፣ የዳልጋ ከብት ቀንድ እና ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የተረፈ ምርት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከሰኔ 01 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚያመርተው በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኝውን እርጥብ ቆዳና ከበጎች እና የፍየሎች የሚገኝው እርጥብ ሌጦ፣ የስጋና አጥንት መኖ፣ የዳልጋ ከብት ቀንድ እና ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡-
- በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ አለበት።
- የጨረታ ማስከበሪያን በተመለከተ ለዳልጋ ከብት የጨረታ ማስከበሪያን የሚሆን ለሦስት የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) እና በወር ውስጥ ለሚገኝው የበግና ፍየል ሌጦ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የዳልጋ ከብት ቆዳ ጨረታ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች የቅድመ ክፍያ ለ10 ቀናት ብር 4,000,000.00 (አራት ሚሊዮን ብር) እና የበግና ፍየል ሌጦ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች የቅድመ ክፍያ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረስኝ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ለስጋና አጥንት መኖ ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ለዳልጋ ከብት ቀንድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) እና ለተነጠረ ሞራ ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ለዳልጋ ከብት ቀንድ ምርቱን በሳምንት ሁለት ቀን እንዲሁም ለስጋና አጥንት መኖ ምርቱ በሚመረትበት በሳምንት ሦስት ቀን (ሰኞ፣ማክሰኞ እና ሐሙስ) እና ለተነጠረ ሞራ ምርቱ በተመረተበት ቀን ሙሉ በሙሉ የእጅ በእጅ ሽያጭ በማከናወን ማንሳት የሚችል መሆን አለበት።
- ምርቱን ለመግዛት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች በጨረታ መመሪያ ላይ በተገለፀው መሰረት ይሆናል።
- አሸናፊው የሚኖረው መብትና ግዴታዎች በውል ውስጥ የሚካተት ይሆናል።
- ከቆዳና ሌጦ ውጪ ላሉት ምርቶች የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይቻላል።
- ጨረታው ለዳልጋ ከብት ቆዳ እና ለበጎች እና ፍየሎች እርጥብ ሌጦ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ለተነጠረ ሞራ ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ለስጋና አጥንት መኖ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም እና ለዳልጋ ከብት ቀንድ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 141 63978 ደውስጡ መጠየቅ ይችላሉ።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት!!!
Tender details
- Deadline: 2026-06-04
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-04 10:30
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Abattoirs Enterprise
- Buyer TIN: 0000028921
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ከቆዳና ሌጦ ውጪ ላሉት ምርቶች
- Published: May 17, 2026
- Posted at: 2026-05-18T10:31:16.000Z
- Buyer website: https://www.aaae.gov.et/en/
Documents
Categories
Products and ServicesAgriculture and FarmingRaw Materials and SuppliesAnimal FeedPoultry, Bee and Animal HusbandryRaw materialsOther SalesSales, Disposals and ForeclosureDisposal SaleShoes and Other Leather ProductsTextile, Garment and LeatherAmharic2merkatoAddis Ababa Abattoirs EnterpriseAddis Ababa
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.