ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. የፋይናንስ እንቅስቃሴ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. የ2017 በጀት አመት አጠቃላይ የተቋሙን የፋይናንስ እንቅስቃሴ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ የኦዲት ድርጅት በጨረታው ላይ እንድትሳተፋ ተጋብዛችኃል።
1. በኦዲት ስራ ፈቃድ ያለው እና የሞያ ብቃት ማረጋገጫ ያለው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የቫት እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው።
3. ተጫራቶች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
4. የኦዲት ሥራው የሚከናወነው በIFRS እና በGAA ሪፖርት አሰራር መሰረት መሆን አለበት።
5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱ ማህተም ማድረግ አለባቸው።
6. በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
7. ማንኛውም ተጫራቾች ኦርጅናሉን የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተቋሙ የፖስታ ሳጥን ቁጥር 2589 ወይም በተቋሙ ኢሜይል አድራሻ Diremicrofinance1996@gmail.com የጨረታ ሰነዱ መላክ ይችላል፤ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታው ሰነድ ገቢ መደረግ አለበት።
8. ጨረታው በተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በተቋሙ በጨረታ ኮሚቴ በይፋ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም።
9. የመክፈቻ ቀኑ የሕዝብ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
10. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 025-112-4820 /
09-35–63-18 73 ደውለው ይጠይቁ
ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ
ድሬዳዋ
Tender details
- Deadline: 2026-06-01
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-01 12:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: Dire Micro Finance Institution S.C.
- Published: May 17, 2026
- Posted at: 2026-05-18T12:15:54.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.