ሕብረት ባንክ አ.ማ. ተሽከርካሪዎች በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥሮች 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል።
|
ተራ ቁ. |
የተበዳሪ ስም |
የአስያዥ ስም |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
የሰሌዳ ቁጥር |
የተሽከርካሪ አይነት |
የስሪት ዘመን |
የሻንሲ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ(ተ.ዕ.ታ. ሳይጨምር) |
ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ስማያዝ ትራንስአክት ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማ/ |
ወይ/ ፌቨን አየለ በላቸው |
በቅሎ ቤት |
አአ-02-01-A36603 |
የመስክ ተሽከርካሪ |
2012 እ.አ.አ. |
JN8BF55S4CT012318 |
HR16*242892C* |
1,739,131.00 |
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት |
|
2 |
አቶ አቡሳድ ነሻ አህመድ |
አቶ አቡሳድ ነሻ አህመድ |
ሕብር ታወር |
አአ-02-C20199 |
የመስክ ተሽከርካሪ- ጃፓን ቶዮታ |
2022 እ.አ.አ. |
JTMAA7BJ1N4023397 |
F33A-0027473 |
23,913,044.00 |
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
የሐራጅ ደንቦች፡-
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ። ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም።
- ተሽከርካሪዎቹን ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ወይም ከቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል።
- የተሽከርካሪዎቹ ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ(ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው።
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ናቸው።
- ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል። ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።
- ተሽከርካሪዎቹ ቀረጥ ተከፍሎባቸዋል።
- ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ተሽከርካሪዎች ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል።
- ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል። ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።
- የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል።
- ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-ክሬዲት ፖርት ፎሊዮና ዴት ሪካቨሪ መምሪያ 011 470 6380/ 011 466 6593 ወይም የሕግ መምሪያ በስልክ ቁጥር 011 470 0315 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
Tender details
- Deadline: 2026-06-01
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-01 12:00
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hibret Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: May 17, 2026
- Posted at: 2026-05-18T13:12:09.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.