እናት ባንክ አ.ማ. ሁለት መኖሪያ ቤት እና አንድ ጂ+3 ጅምር ሆቴል ባሉበት ሁኔታ በድርድር ሽያጭ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የድርደር ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- አባ ንሃ/06/2016

እናት ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ላይ የተዘረዘሩትን ሁለት መኖሪያ ቤት እና አንድ ጂ+3 ጅምር ሆቴል በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ባለበት ሁኔታ በድርድር ሽያጭ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ ከታች በቀረቡት ዝርዝር ማብራሪያዎች መሰረት በድርድር ሽያጩ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

ተ.ቁ

የቦታው አገልግሎት

ለድርድር የቀረበው ንብረት የሚገኝበት አድራሻ

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

የቦታው ስፋት

1

መኖሪያ ቤት

አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 10

18/60/64/52/

27310/54641/

60134/03

240.75 ሜትር ካሬ

 

2

መኖሪያ ቤት +1

ኦሮሚያ፣ ሰንዳፋ በኬ፣ ቀበሌ 01

447/834/98

 

200.00 ሜትር ካሬ

 

3

ጅምር ሆቴል +3

ኦሮሚያ ፣ሞጆ ከተማ፣ 02 ቀበሌ፣ አፍሪካ ማደያ ፊትለፊት

3731/2000

 

1800.00 ሜትር ካሬ

 

ማሳሰቢያ

1. በድርድር ጨረታዉ የቀረቡትን ንብረቶች ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከማቅረባቸው በፊት ከባንኩ ጋር አስቀድመው ቀጠሮ በመያዝና ማየት ይችላሉ።

2. ገዥዎች የድርድር ጨረታ አካሄድ ዝርዝር መመሪያ የያዘውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ካዛንችስ እናት ታወር ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ግዥ እና ፋሲሊቲ ሥራ አመራር መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 575 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር) ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

3. ገዥዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለመግዛት የሚያቀርቡትን ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (ሲ.ፒ.ኦ) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ገዥዎች ንብረቱን ለመግዛት የሚሰጡትን ዋጋ ጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ካስፈሩ በኃላ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝ ካዛንችስ እናት ታወር ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ግዥ እና ፋሲሊቲ ሥራ አመራር መምሪያ ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ከግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታዉ ሰኔ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ዓ.ም ይዘጋል:: በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት 7ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

6. የድርድር ጨረታዉ አሸናፊ ሊዝ እና ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈለውን ማናቸውም ክፍያዎች ይከፍላል።

7. የድርድር ጨረታዉ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል።

8. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-5585014 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

ማን እንደ እናት

ማሳሰብያ በአንድ የጨረታ ሰነድ መጫረት የሚቻለዉ ለአንድ ንብረት ብቻ ነዉ።


Tender details

  • Deadline: 2026-06-10
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-06-10 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Enat Bank S.C.
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር)
  • Published: May 17, 2026
  • Posted at: 2026-05-18T13:40:29.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders