Poultry, beekeeping and animal feed
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ሆርሞን እና የዓሳ መኖ ህጋዊ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር 06/2018
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ሆርሞን እና የዓሳ መኖ ህጋዊ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
1) በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፤ጨረታ መሳተፍ የሚችልና የምዝገባ ምስክር ወርቀት ማቅረብ የሚችል የምትችል
2) ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ባንክ በማስገባት ከመ/ቤቱ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከጎርጋዳ ሰፈር ከፍ ብሎ ሲዳማ ብ/ክ/መ/ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 በአካል ሆነ በተወካዮቻቸው አማካይነት መግዛት ይቻላል።
3) በየዘርፉ የጨረታ ማስከበሪያ(Bid Bond) ብር 20,000(ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና/Bank GAURANT/ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ። የጨረታ ማስከበሪያ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።
4) አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት።
5) ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል)እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም ሁሉም በመምታት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን (ተከታታይ ቀናት) ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በአስራ ስድስተኛው ቀን ሰነድ መሸጥና መግዛት አይቻልም።
6) ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ላይ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም።
7) መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
8) መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅት ህጋዊ ማህተም ሳያደርግ የቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
9) የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
10) የሰነድ ማስገቢያ ከመጨረሻው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ አመልካቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
11)ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 16 10 83 60/ 09 16 07 00 57 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- ከጎርጋዳ ሰፈር ከፍ ብሎ በሲዳማ በሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 እንገኛለን።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-06-02
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን (ተከታታይ ቀናት) ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-02 14:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን (ተከታታይ ቀናት) 8፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama National Regional State Livestock Resource Development Bureau
- Buyer address: ከሳውዝ ኢንተርናሽናል ሆቴል ከፍ ብሎ ደቡብ ግሎባል ባንክ ባለው ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (May 18, 2026)
- Posted at: 2026-05-19T09:02:31.000Z