የኢትዮጵያን ሸ/ኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር የማህበሩን የ2015 በጀት ዓመት መነሻ በማድረግ የ2016 እና የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የኦዲት ስራ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ሁለተኛ ጊዜ የወጣ የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር፡- ኢ/ሸ/ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ/22113/18/ዓ.ም

የኢትዮጵያን ሸ/ኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር የማህበሩን የ2015 በጀት ዓመት መነሻ በማድረግ የ2016 እና የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የኦዲት ስራን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ዓመታዊ ሂሳብ ሪፖርቱን ኦዲት ማሰራት ይፈልጋል። 

ተጫራቾቹ

1. የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም እሱ ከሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለውን የሙያ ፈቃድ ያገኘ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት መቅረብ የሚችል/የምትችል፤

2. የህብረት ስራ ማህበራት ሂሳብ ምርመራ በተመለከተ ከፌዴራል ህብረት ስራ ኤጄንሲ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኤጄንሲ ወይም ከሌሎች ህጋዊ አካላት ስልጠና የወሰደና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ቢሆን ይመረጣል፤

3. በመሰል ማህበራት ውስጥ የኦዲት ስራ ስለመስራቱ የልምድ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፤

4. ተጫራች ቀጥሮ የሚያሰራቸውን ባለሙያዎች ሂሳቡን ለመመርመር የሚያስችላቸውን ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::

5. ተጫራቾች የመልካም ስራ አፈፃፀም መረጃዎቻቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤

6. ማህበሩ ኦዲት ስራ ያቀረበው ሰነድ ብዛት 22 ፎልደር ወጪና 25 ፎልደር ገቢ በድምሩ 47/ አርባ ሰባት/ሲሆን ሙሉ በሙሉ ዝርዝር ኦዲት ይደረጋል።

7. ተጫራች ኦዲት ስራውን የሚሰራበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ስርዝ ድልዝ ሳይደረግ ግልፅ በሆነ መልኩ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያ ከወጣበት በ7 የስራ ቀናቶች ውስጥ ቅዳሜ እስከ ቀኑ 6፡30 ድረስ መጠቀም ይችላሉ። ጨረታው በ7ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡15 ላይ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የኢትዮጵን ሸ ኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር ግዥ ክፍል ይከፈታል። 7ኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ቀን ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉለውም።

8. ተጫራቾቹ የተጫረቱበትን የጨረታ ውል ማስከበሪያ ዋጋ 2% የኢትዮጵን ሸ/ኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር ስም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ ሲፒኦ ወይንም ቢዲ ቦንድ ማሰራት ወይንም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000280343548 ማስገባት ይጠበቅባችዋል።

9. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከታች በተገለጸው አድራሻ ማለትም ኢትዮጵያን ሸ/ኃላ/የተ/የህ/ማህበር ቢሮ ያለ ክፍያ ተመዝግቦ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።

10. በጨረታ አፈፃፀሙ ቅር የተሰኘ አካል በቅሬታው መሰረት የሆነውን የመጨረሻ ውሳኔ ካወቀበት ወይም ማወቅ ከነበረበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ በጽሁፍ ለተቋሙ ማናጀር ማቅረብ ይጠበቅበታል። ሆኖም ከተጠቀሰው ቀን በኋላ፤ የሚቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ።

11. ተጫራቾቹ በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማስገባት ከጨረታ ውድድሩ ያሰርዛል።

12. አሸናፊው ድርጅት የኢትዮጵን ሸኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር ጋር ውል በመግባት መስራት ይጠበቅበታል።

13. ከላይ ከተዘረዘሩት መስፈርቶችን አሟልቶ በዋጋ እኩል ያመጣ ተወዳዳሪ ለማህበሩ አባል ከሆነ በቅድሚያ ይሰጣል። የማህበሩ አባል ካልሆኑ በዕጣ ይለያል።

14. የሸማች ህ/ስ/ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፤ ከ49 ማዞሪያ ወደ አራብሳ በሚወስደው አስፓልት ሎሚ ከለር 40/60 ኮንደሚኒየም መጨረሻ በግምት 200 ሜትር ተጉዘው ኢትዮጵያን አየር መንገድ ሰራተኞች የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ ያገኙታል።

በስልክ ቁጥር 09-11-29-17-17/ 09-30-33-33-98 /09-12-97-51-94 ወይም 09-07-50–97-07 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ኢትዮጵያን ሸ/ኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-05-25
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ ከወጣበት በ7ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-05-25 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያ ከወጣበት በ7ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የኢትዮጵያን ሸ/ኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር
  • Bid bond: 2%
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-19T09:14:00.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders