Disposal, scrap and surplus sales

የካፋ ልማት ማኅበር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ በማህበሩ የእንግዶች ማረፊያ ተቋም፣ በኃኪዮን የመኪናዎች ጥገናና ሰርቪስ ጋራዥ ግቢ ውስጥ እና በቦንጋ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ በተለያዩ ጊዜያት አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ አሮጌ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የካፋ ልማት ማኅበር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ በማህበሩ የእንግዶች ማረፊያ ተቋም፣ በኃኪዮን የመኪናዎች ጥገናና ሰርቪስ ጋራዥ ግቢ ውስጥ እና በቦንጋ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ በተለያዩ ጊዜያት አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ አሮጌ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

 የንብረቶችን መለያ በሚመለከት፣-

  • ሎት-1 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ማለትም ዲፌንደር መኪና፣ ማርቸዲስ መኪና፣ ዶዘር ወዘተ
  • ሎት-2 የተለያዩ አሮጌ ብረታ ብረቶች ሲሆኑ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ማንነታችሁን የሚገልጽ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ/ፋይዳ ወይንም የቀበሌ መታወቂያ በመያዝ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በመሆኑም ከላይ በተገለፀው መሠረት የሎት -1 ተጫራቾች የባንክ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም የሎት-2 ተጫራቾች ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ የባንክ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ተጫራቾች ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በቦንጋ ከተማ በሚገኘው በካፋ ልማት ማህበር ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት የጨረታውን ዶክመንት በብር 500 ብር /አምስት መቶ ብር/ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ጨረታው በቀጣዩ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 047 331 0420 ወይንም በሞባይል ቁጥር 09 17 53 43 81/ 09 11 59 68 29 በመደወል መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።

የካፋ ልማት ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-06-04
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-06-05 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:30
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Kefa Development Association
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (May 19, 2026)
  • Posted at: 2026-05-19T12:45:57.000Z
← Back to all tenders