አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ብሔራዊ ግልፅ

የጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

1. የ2018 ዓ.ም ህጋዊና በማንኛውም ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።

2. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለየሎቱ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ሂሳብ ቁጥር 1000007971544 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እየከፈሉ ደረሰኝ በማቅረብ ከታች በተገለጸው አድራሻ ህንፃ ቁጥር 86 ቢሮ ቁጥር 001 ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

3. ጨረታው ባለ አንድ ፖስታ በመሆኑ ሰነዳቸውን (የዋጋና የህጋዊነት ሰነድ) በአንድ ፖስታ በግማሽ፣ ከኦርጅናሉ በተጨማሪ አንድ ቅጅ በሌላ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ መሆኑን በፖስታ ላይ በመግለፅ በመጻፍ የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውሰጥ ከታች በተመለከተው አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ተከታታይ 10 ቀናት በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በንብረት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ ህንፃ ቁጥር 86 ምድር ወለል ላይ በሚገኘው ቢሮ ይከፈታል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚከተለው ለተወዳደሩበት ምድብ ለየብቻ ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

1ኛ፡- ያገለገሉ የቢሮ ፈሪኒቸሮች ሽያጭ ብር 10,000

2ኛ፡- ያገለገሉ ብረት ነክ እና ፕላስቲክ ስሪት የሆኑ ሽያጭ ብር 10,000

3ኛ፡- ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች እና ባትሪ ሽያጭ ብር 10,000

4ኛ፡- ያገለገሉ የተለያዩ ቶነሮችና ካርትሌጆች ሽያጭ ብር 5,000

6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ቀናት ነው።

7. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-30
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-30 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Science and Technology University
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር በየሎቱ
  • Published: May 20, 2026
  • Posted at: 2026-05-20T08:53:37.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders