የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተለያዩ የደንብ ልብሶች ግዥ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ፌ.ቤ.ኮ/ ብግጨ /ዕግ/43/09/2018
- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተለያዩ የደንብ ልብሶች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕግ/43/09/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋ።
- ኮርፖሬሽኑ ለሚፈጽመው የተለያዩ የደንብ ልብሶችን ግዥ ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነዳቸውን እና የዋጋ ሰነደቸውን በአንድ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ መመሪያ ቁጥር 1070/2017 በፌድራል መንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።
- የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው በቀድሞ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 209 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሁለተኛ ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ወይም ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/፤ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር ናሙናዎችን አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤ ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ ከውድድር ውጭ የሚደረግ ይሆናል።
- ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተደደር ዳይሬክተር 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት አሸናፊው ተጫራች በኮርፖሬሽኑ በግንባር በመገኘት ዕቃዉን ያስረክባል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 011-1-855-3667 ደውሉ መጠየቅ ይቻላል።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-06-03
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-03 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Housing Corporation
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: May 20, 2026
- Posted at: 2026-05-20T09:29:09.000Z
- Buyer website: https://www.fhc.gov.et
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.