በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ ኮምፕዩተሮች ላፕቶፖች፣ የቢሮ ወንበር እና ጠረጲዛ እንዲሁም የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ዕቃዎች የጨረታ ሠነድ 001/2018

በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ አገልግሎት መስጠት የማይችሉ የመንግሥት ቋሚ ንብረቶች

  • ኮምፕዩተሮች ላፕቶፖች፣
  • የቢሮ ወንበር እና ጠረጲዛ እንዲሁም
  • የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እና
  • ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ ለመሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. ተጫራቾች ለ2018 ዓ.ም ከዘርፉ ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም የዘመኑ ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) ብቻ በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ስም በተከፈተው በኢት/ንግድ/ባንክ ቁጥር 1000640119377 ገቢ በማድረግ የባንክ አድቫይስ በማምጣት በኮሌጁ ግዥ ዴስክ ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት መውስድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ንብረቶቹን በማንኛውም የመንግሥት የሥራ ሠዓት በኮሌጁ ግምጃ ቤት በመምጣት በአካል መመልከት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የሚጨረቱበትን የንብረቱን ጠቅላላ ዋጋ  በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመሙላት የድርጅታችሁን ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ ማስቀመጥ ይኖርባችኋል።
  5. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ አድርገው ግንቦት 27/2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኢ/መ/ዩ/ኢ/ኮሌጅ ውስጥ በሚገኘው ግዥ ዴስክ ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ግንቦት 27/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ግዥ ዴስክ ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ጨረታው ሳይከፈት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ለጨረታ ያስያዙትን ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊ ከታወቀ ወዲያውኑ ለተሸናፊዎች የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊ ድርጅት ግን ንብረቶቹን ጨርሶ ሲያነሳ የሚመለስለት ይሆናል።
  9. አሸናፊ ድርጅት የአሸነፈባቸውን ዕቃዎች በአጠቃላይ የማንሳት ግዴታ አለበት።
  10. ኮሌጁ ለአፈፃፀም የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ቢሾፍቱ በቀጥታ ስልክ ቁጥር-011 433 8400 የውስጥ መስመር 276 እና 274 ጠይቆ መረዳት ይችላል።
  12. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎችን የነጠላ ዋጋ መስጠት አይቻልም። አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ድምር ነው።
  13. ተጫራቾች የመንግሥት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ (EGP)ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-04
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-04 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Defense University Engineering College
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 20, 2026
  • Posted at: 2026-05-20T09:36:57.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders