ወጋገን ባንክ አ.ማ. ፒክአፕ መኪና በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር፡ ወጋገን 025/2018
ወጋገን ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሰረት ከዚህ በታች የቀረበውን የመያዣ ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
ንብረት አስያዥ |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
የተሽከርካሪ ዓይነት |
የሰሌዳ ቁጥር |
የሻንሲ/ሴሪያል/ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
ዘመን |
የነዳጅ አይነት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ጨረታው የሚከናወንበት ቀን |
|
|
ቀን |
ሰዓት |
|||||||||||
|
1 |
ኤን ኬይ ኤች ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
ተበዳሪው |
ሰባራ ባቡር |
ድርብ ተግባር (ፒክአፕ) |
አአ-03-B33009 |
MR0DB9CD7M5151328 |
2GD-5010093 |
2021 |
ናፍጣ |
3,800,000.00 |
ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም |
ከጧቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት |
ማሳሰብያ
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት በመቅረብና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታ አሸናፊ ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
- በጨረታው አሸናፊ ለሆነ፤ የባንኩን የብድር ፖሊሲ፤ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟላ ተጫራች ባንኩ በውስጥ መመሪያ መሰረት ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- የተጫራቾች የምዝገባ ሰዓት፤ ከጧቱ 3፡00 – 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው ይቀጥላል።
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ካካሄደው ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
- ጨረታው የሚካሄደው፡ በወጋገን ባንክ ዋና መስርያ ቤት 13ኛ ፎቅ ባለው የመሰብሰብያ አዳራሽ ይሆናል።
- ለሀራጅ ጨረታ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፊት ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል።
- ተበዳሪው /ንብረት አስያዥ/ ወይም ሁለቱም በጨረታው ቀን እና ሰዓት በቦታው ላይ መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ተበዳሪው /ንብረት አስያዡ/ በጨረታ ቀን እና ሰዓት በቦታው ባይገኝ ጨረታው በሌለበት ይካሄዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው።
- ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል።
- ለበለጠ ማብራሪያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት ወጋገን ባንክ አ.ማ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት 011-558-18-37፣ መደወል ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ወጋገን ባንክ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-06-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-06-04 12:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Wegagen Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: May 20, 2026
- Posted at: 2026-05-20T13:14:20.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.