የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ያገለገሉ መኪና፣ ሞተር ሳይክሎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና ኤሌክትሮኒክስ
ሽያጭ ማስታወቂያ

የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞን አስተዳደር ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ ያገለገሉ መኪና፣ ሞተር ሳይክሎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች።

1. መኪኖች፣ ሞተር ሳይክሎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የሚገኙበት አድራሻ ዞን እስተዳደር ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸውን ከማቅረባቸው በፊት መኪኖች፣ሞተርሳይክሎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት በአካል በመገኛት ከላይ በተገለፀው አድራሻ አስቀድመው ማየት የሚችሉ ሲሆን በጨረታው ሰነድ ላይ ካለው መረጃ በአካል ቀርበው ሲመለከቱ ልዩነት ካለ እና ይህንኑ ሲያረጋግጡ ጨረታው ከመዘጋቱ ከ5 የሥራ ቀናት በፊት ለመምሪያው ማሳወቅ አለባቸው።

3. በጨረታው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለስብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል።

4. ተጫራቾች የሚገዙበትን የተሽከርካሪ ኤልክትሮኒክስ በጨረታ መነሻ መግዥያ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ከውድድሩ ቢወጡ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታው ያሸነፈ ተጫራች እንደተመረጠ ወዲያውኑ ጨረታውን ላላሸነፉ ተጫራቾች በቀጣይ 5 የሥራ ቀናት ተመላሽ ይደረጋል።

5. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን የመኪና፣ የሞተርሳይክሎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ዝርዝር መረጃ የያዘ ሰነድ ይህ ማታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ በመምሪያው ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 2 ለያንዳንዱ የማይመለስ 400 መቶ ብር በመክፈል ሰነዱ መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ተሸከርካሪ እና ኤልክትሮኒክስ ዋጋ በታሸገ ኢቨሎፕ 1 ኦርጅናል እና ኮፒ በማዘጋጀት ከላይ ሙሉ አድራሻውን በመጻፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት ውስጥ ከቀኑ 11፡30 በመምሪያው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣ በ16ኛው የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ የሚከፈት ይሆናል።

8. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉበት ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች እና የኤልክትሮኒክስ ሙሉ ክፍያውን በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ማንሳት አለባቸው በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።

9. መምሪያው የተሻለ መንገድ ካገኛ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ 0912 122 421
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-08
  • Publishing entity: Halaba Zone Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: የተሽከርካሪ እና ኤሌክትሮኒክስ 10%
  • Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: May 21, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders