በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ለሚገኘው መካከለኛ ክሊኒክ ለህክምና አገልግሎት የሚውል የመድሃኒት አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ለሚገኘው መካከለኛ ክሊኒክ ለህክምና አገልግሎት የሚውል የመድሃኒት አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው።
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸዉ።
- የሚገዙ የመድሃኒት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመከፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት አቅርቦት ጠቅላላ ድምር ውጤት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ አንድ በመቶ ማስያዝ አለባቸዉ።
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅ በፖስታ ማለትም ኦርጅናልና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግን/ን/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሠዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከግንቦት 10/2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም 11፡00 ድረስ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሆነ ባይገኙም ጨረታው በሰዓቱ በግ/ፋ/ን አስ/ቡድን ቢሮ ግንቦት 25/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋይ/ንብ/አስ/በድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 73 44 61/09 64 79 28 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-06-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-02 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: May 18, 2026
- Posted at: 2026-05-21T09:13:13.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.