የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ባለስልጣን ከተዘጉ ድርጅቶች እና ለፈንድ ማጠናከሪያ ድጋፍ ካደረጉ ድርጅቶች ላይ ያገኛቸውን ያገለገሉ ንብረቶች እነሱም ተሸከርካሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የተለያዩ የቢሮ እቃዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የህክምና እቃዎች፣ ጄኔሬተር፣ ሶፋ እና የመሳሰሉትን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ባለስልጣን ከተዘጉ ድርጅቶች እና ለፈንድ ማጠናከሪያ ድጋፍ ካደረጉ ድርጅቶች ላይ ያገኛቸውን ያገለገሉ ንብረቶች እነሱም ተሸከርካሪ፣ኤሌክትሮኒክስ፣የተለያዩ የቢሮ እቃዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የህክምና እቃዎች ፣ጄኔሬተር፣ ሶፋ እና የመሳሰሉትን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ኤፍ አካውንት ቁጥር 1000332121708 እየከፈሉ ከተቋሙ ግዢና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ 11፡00 ሰዓትድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን በአስራ አንደኛው ቀን ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መሆኑን እናሳውቃለን።

2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በሚል ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡አሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ ከፍለው ሲመጡ ተመላሽ ይሆናል፤ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት በጨረታ አፅዳቂ መፅደቁ ወይም ውድቅ መሆኑ በማስታወቂያ ከተገለጸ በኋላ ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል።

3. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 10 ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ጨረታው 4፡00 ተዘግቶ 4፡15 የሚከፈት ይሆናል።

4. ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመግዛት ከሰነዱ ላይ ሙሉ ዝርዝሩን ያገኛሉ።

5. የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ አዲስ አበባ ከተማ ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ህብረት ኢንሹራንስ ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 608 በመገኘት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣

6. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

7. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን ንብረቶች የሚገኙበት ቦታ ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አለፍ ብሎ ከአድማስ ዩኒቨርስቲ አጠገብ በስተቀኝ በሚያስገባው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ ኒያላ ኢንሹራንስ የተጎዱ መኪኖች ማቆያ ፊት ለፊት በሚያስገባው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ተቋሙ በተከራየው መጋዘን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 9፡30 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፤

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር-011-558-24-37 / 011-558-23-76/ 09-01-19-09-39 / 09-61-71-26-04

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-01
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 10 ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ጨረታው 4፡00
  • Bid opening: 2026-06-01 10:15
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 10 ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ጨረታው 4፡15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Civil Society Organization Authority
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 21, 2026
  • Posted at: 2026-05-21T09:25:42.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders