Disposal, scrap and surplus sales
ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ያገለገሉ እስቴል ብረት፣ ያገለገሉ ካስትል አይን ብረት፣ ያገለገሉ የአልሙኒም ብረት እና ያገለገሉ የተሽከርካሪ/ማሸነሪ መለዋወጫ ብረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በስሩ የሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች እስቶር ውስጥ የሚገኝ
- 1ኛ ያገለገሉ እስቴል ብረት፣
2ኛ ያገለገሉ ካስትል አይን ብረት፣ - 3ኛ ያገለገሉ የአልሙኒም ብረት፣
- 4ኛ ያገለገሉ የተሸከርካሪ /ማሸነሪ መለዋወጫ ብረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ግለሰብ (ድርጀት) በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- መነሻ ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የዕቃ አይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ማለትም በአማረኛ የተተረጎመ፣ ሲፒኦ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከግንቦት 10/2018 ዓ/ም እስከ ግንቦት 24/2018 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ከግንቦት 10/2018 ዓ/ም እስከ ግንቦት 24/2018 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን ግንቦት 25/2018 ዓ/ም 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጃናሞራ ወረዳ ከስድስቱ ንብረት ክፍል ሲሆን አጣቃላይ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሲሆን እቃውን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ትራንስፖርት እንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-02 10:15
- Region: Amhara
- Publishing entity: Janamora Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: 200,000 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Be'kur (May 21, 2026)
- Posted at: 2026-05-21T09:28:11.000Z