የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የካራቆሬ ስቶር የሼድ ወለል/የመሬት ስራ፣ የትራንስፎርመር ማስቀመጫ የሃርድ ኮር (ማሻሻታ) እና የኮንክሪት ወለል አገልግሎት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EEU/PPMNCB/15/2018

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የካራቆሬ ስቶር የሼድ ወለል/የመሬት ስራ፣ የትራንስፎርመር ማስቀመጫ የሃርድ ኮር (ማሻሻታ) እና የኮንክሪት ወለል አገልግሎት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
  2.  የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የኢኤአ ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት በማህበራዊ ዋስትና ህንፃ ከ11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በግዥ ፈጻሚው መ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 175,000.00 (አንድ መቶ ሰባ አምስት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኃላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለው የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በኢኤአ ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ወይም EEU-PPM ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ እና ጨረታ ቁጥር EEU/PPM NCB/15/2018 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዋስትና የንግድ ማዕከል ህንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በግዥ ፈጻሚው መ/ቤት በመምጣት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  5.  የጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከ ቀኑ 8.30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  6. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ከ ሰዓት 7፡00 –11፡00 እና ቅዳሜ ጠዋት ከ 2፡00 – 6፡00 መመልከት ይቻላል።
  7.  የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 011-1-26-31-53 መደወል ይችላሉ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-05
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-06-05 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
  • Bid bond: 175,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: May 22, 2026
  • Posted at: 2026-05-22T07:53:34.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders