የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም የተለያዩ ዓይነት ዕቃዎችን ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
Description
ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ለ2019 በጀት ዓመት ከሐምሌ 01/2018 እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ/ም ድረስ በሥራ ላይ የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት ዕቃዎችን –
ሀ/የሕግ ታራሚዎች መኖ እህል ዓይነቶች
ለ/ የህግ ታራሚዎች መኖ ምግብ ማጣፈጫዎች
ሐ/የመኖ ምግብ ማብሰያ ማገዶ እንጨት
መ/ አጥንት የሌለበት ቀይ የከብት ሥጋ
ሠ/ የተለያዩ የቢሮ ጽህፈት መሳሪያዎች
ረ/ለተማሪዎች መማሪያና ማስተማሪያ ጽ/መሣሪያ እንድሁም ማጣቀሻ መጽሃፍት
ሰ/ የጉልበት ሠራተኞችና የሀኪሞች የሥራ ልብስ ማንቺንና ነጭ ጓንት እና የሥራ ቱታዎች የተዘጋጁ
ሸ/የተለያዩ የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች
ቀ/ የተለያዩ የማብራት ዕቃዎች
በ /ለመ/ቤቱ ዙሪያ አጥር ጥገና የባህረ ዛፍ ግድግዳ ፣ ማገር ፣ መሪ
ቨ/ ለታራሚዎች ለተለያዩ ሥልጠና የሚውሉ ፣ ብረታብረት ፣ ግንባይኝነት ፣ ብሎኬት ሥራና ለአናጽነት የሚያገልግሉ ፣ ቱቡላሬ ፣ ላሜራ ኤሌክትሮድ ፣ አሸዋ ፣ ዲንጋይ ፣ ሲሚንቶ ፣ ቀለም ፣ ኮላ ፣ ስቱኮ፣ ሚስማር ፣ የባህርዛፍ ውጤቶች ፣ የተለያዩ ዓይነት ቆርቆሮች እና ሌሎችን የህንጻ መሳሪዎች
ተ/ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ኮምፒተር ከነፐርተርና ፕሮጀክተር የመሣሰሉትን
ቸ/ ፌርንቸር/ የቢሮ ቋሚ ዕቃዎችን
ኀ/ ለታራሚዎች ሥልጠና የሚውሉ የተለያዩ የእንጨት ውጤቶች ጣውላዎች፣ ኮምፐርሳቶዎች፣ ፋይዜቶችና ሌሎች
ለስራው የሚያገለግሉ ዕቃዎች ሲሆን በየዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ነጋዴዎችን እና ከአደራጅ መ/ቤት የብቃት ማረጋገጫ ድጋፍ ያላቸውን የፋይናንስ ደንብና መመሪያ አሟልተው የሚቀርቡ የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራትን ጨምሮ በማጫረት ከአሸናፊዎች ጋር ውል ተዋውሎ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች ለጨረታ ሲቀርቡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ለአሸናፊው ግን ከውል ማስከከበሪያ ዋስትና ጋር የሚታሰብ ለመኖ እህል ብር 200000.00/ ሁለት መቶ ሽህ ብር/ ለመኖ ማጣፈጫና ለማገዶ እንጨት ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና ከላይ ለተዘረዘሩ ለሌሎች ለእያንዳንዳቸው ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፡ ብር 5,000.00/ አምስት ሺህ ብር፣ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ከየጨረታው ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዞ በፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሁሉም ጨረታዎች የተዘጋጀውን የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በማይመለስ ብር 50/ሀምሳ ብር በመክፈል ከመ ቤታችን ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይፋ ከሆነበት ቀን አንስቶ በተከታታይ ለ15 ሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- በጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ዋስት 10 አሸናፊነቱ በተረጋገጠ በ10 ቀናት ውስጥ አሸናፊው ዕቃ ዓይነት ባሸነፈው ዋጋ ስልቶ 10% ለማስያዣ ፈቃደኛ ካልሆነ እና አሸንፎም አላቀርብም ካለ ለጨረታው ዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለመንግስት ውርስ ይደረጋል።
- ከላይ ከፊደል ተራ ሀ / እስከ ኀ/ ድረስ የተዘረዘሩ ዕቃዎች ዓይነት ፣ መለኪያና መጠን/ ብዛት ዝርዝር በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በዝርዝር ተካቶ ይቀርባል።
- አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ተጫራቾች ለተዘረዘሩት ዕቃዎች በውድድሩ ቀን ናሙናውን ይዞ መቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውንና የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሥራ ሰዓት እስከ ጨረታ ማበቂያ ቀን 7፡30 ድረስ በጨረታው ሳጥን መጨመር ይኖርባቸዋል።
- ሁሉም ዕቃዎች ጨረታ ሳጥን ተዘግቶ የሚከፈተው በዕለቱ ከ7፡30 ሰዓት ድረስ በተቋሙ ቅጥር ግቢ በቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ተጨምሮ በ7፡35 ሰዓት ተዘግቶ ሁሉም ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል። ግን ዕለቱ የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
- የእህል ተጫራቾች ለመ/ቤታችን የዕቃዎች ማከማቻ መጋዘንና ቦታ ስለሌለው የቀጣዩን ወር በገባ እስከ 20ኛው ቀን ድረስ ተጠቃሎ ገቢ ሲያደርጉ የቀድሞ ወር ክፍያው ግን ወር በገባ እስከ 28ኛው ቀን ደረስ የሚፈጽም መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዕቃ ዓይነት በራሳቸው መጓጓዣ በማምጣት በመ/ቤቱ ቅጥር ግቢ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ አቅራቢዎች በዕቃዎች አቀራረብ ላይ የጥራትና የማስተጓጐል ችግር ቢፈጠር ለውል ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከመቀጣቱም በተጨማሪ ለተፈጠረው ችግር በሕግ ፊት ተጠያቂ ይሆናል:: ከላይ በፊደል ሀ እና ለ የተገለፁት መኖ እህል እና መኖ ማጣፈጫዎች በማዕቀፍ ውል መሠረት በየሦስት ወሩ ከኢትዮጵያ መረጃ ስታትክስ ዕቃዎች ዋጋ መነሻ ከደቡብ አ/ክ/መ/ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን በፈቀደው መሰረት የዋጋ ለውጥ ከጨመረ በመጨመር ከቀነሰ በመቀነስ የዋጋ ለውጥ ካለ ቀድሞ በገባው ውል ዋጋ የሚቀጠል ሆኖ የዋጋ ለውጥ ይደረጋል።
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ/በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፤- 0465512117/ 0916107578/ይጠይቁን
የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም
Tender details
- Deadline: 2026-06-08
- Bid closing time: 13:35
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይፋ ከሆነበት ቀን አንስቶ በተከታታይ ለ15 ሥራ ቀናት ውስጥ 7፡35 ድረስ
- Bid opening: 2026-06-08 14:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይፋ ከሆነበት ቀን አንስቶ በተከታታይ ለ15 ሥራ ቀናት ውስጥ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Wolaita Sodo Correctional Facility
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 50.00 ብር
- Published: May 22, 2026
- Posted at: 2026-05-22T08:01:39.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.