በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት የቀበና ጤና ጣቢያ የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር መድሃኒት፣ የላብራቶሪ ሬጀንቶች እና አላቂና ቋሚ የሕክምና ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት የቀበና ጤና ጣቢያ የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር

በጨረታ ቁጥር ቀ/ጤ/ ጣቢያ 3/2018 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ መድሃኒት፣ የላብራቶሪ ሬጀንቶች ፣ አላቂና ቋሚ የሕክምና ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የጨረታ ግዥ መለያ ቁጥር የቀ/ጤ/ጣ/03/2018 ዓ.ም

ሎት 1 መድሃኒት፣ የላብራቶሪ ራኢጅነቶች አላቂና ቋሚ የሕክምና ዕቃዎች

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ቫት ተመዝጋቢ የሆነ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስተር በአቅራቢነት የተመዘገቡና የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ቲን ነምበር ያላቸው።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀበና ጤና ጣቢያ ፋይናንስ ክፍል ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ 6,000.00 /ስድስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒአ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን ለማስገባት በሚመጡበት ጊዜ ሳምፕል ለሚያፈልጋቸው ዕቃዎች ሳምፕል አብሮ ማስገባት አለባቸው ፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን ከሲፒኦ ጋር በአንድ ፓስታ ኮፒ ሰነድ በሌላ ፓስታ አሽገው የድርጅቱን ማህተብ በማድረግና በፊርማ በማረጋገጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30- 6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 -11፡00 ሰዓት የጤና ጣቢያው የግ/ን/አስ/ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡የጨረታው ሳጥን በ 11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ በቀበና ጤና ጣቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የአንዱ ዋጋም ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ሲቀመጥ ሻት አካቶ መሆን አለበት።
  7.  ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራቾች በተመዘገቡበት ንግድ ፍቃድ ዘርፉ ብቻ መወዳደር አለባቸው።
  8. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ ውል ከተፈራረመበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ እስከ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርበታል።
  9. በዚህ አንቀጽ በተገለፀው መሠረት ዕቃዎቹን ያላስገባ ካሸነፈበት ጠቅላላ ብር ላይ በእለቱ 0.01 ተቀናሽ እንደሚደረግ እናሳስባለን፡፡ የገዙትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የመጣ ማንኛውም ስነድ ተቀባይነት የለውም ።ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-አድራሻ ቀበና የኦሮሚያ ደን ልማት ሕንፃ ገባ ብሎ ቀበና መድሀኒዓለም ቤተክርስቲያን አጠገብ ነው።

ስልክ ቁጥር፡-011  8-11  21 55

0111  23 56 07 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት የቀበና

ጤና ጣቢያ የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር


Tender details

  • Deadline: 2026-06-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-03 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Arada Sub City Kebena Health Care Office
  • Buyer address: ቀበና ሼል ከመድረሱ በፊት የኦሮሚያ ድን ህንፃ ገባ ብሎ ቀበና ምሥራቅ ፀሐይ መድሃኒያዓለም ቤተክርስቲያን አጠገብ
  • Bid bond: 6,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 22, 2026
  • Posted at: 2026-05-22T08:05:26.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders